Get Mystery Box with random crypto!

​​ወንድ ሆይ ሴት ልጅ ካንተ ምን ትፈልጋለች :- ➊ ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገ | ፍቅር እና ህይወት

​​ወንድ ሆይ ሴት ልጅ ካንተ ምን ትፈልጋለች :-

➊ ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት ፡፡

➋ ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች ። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል።

➌ ሴቶች ግትር ወንዶችን
ይጠላሉ። ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ፡፡ አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።

➍ ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ፡ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ።

➎ ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው። ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል። በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም። ከንግስና ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር። ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

➏ ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም።
አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ
ለማድረግ አትጣር። ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

➐ ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ። ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ። ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው።ልታቃናት ከሞከርክ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት። መካከለኛ ሰው ሁንላት።

➑ ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ነገር ግን እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት። ይህን
ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ ።

➒ ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል። SO ትእዛዝ አታብዛባት።

➓ ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን
አትዘንጋ። ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት፡ እዘንላት፡ በድክመቷ (የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት። ምርጥ የሂዎት አጋርህ
ትሆናለች።

መልካም ቀን

@Sura16722