Get Mystery Box with random crypto!

የቻይና ወታደሮች ለጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሩሲያ ገቡ በዚህ ሳምንት ሩሲያ በሚካሄደው የቮስቶክ 2 | Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ

የቻይና ወታደሮች ለጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሩሲያ ገቡ

በዚህ ሳምንት ሩሲያ በሚካሄደው የቮስቶክ 2022 ስትራቴጂካዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የሚሳተፉ አገራት ወታደራዊ ቡድኖች ወደ ሩሲያ መድረሳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሰኞ ዕለት አስታውቋል።

ከሩሲያ ጦር ኃይሎች በተጨማሪ የቻይና, ቤላሩስ, አዘርባጃን, አርሜኒያ, ሶሪያ, ህንድ እና ሌሎች ተባባሪ አገራት ወታደሮች ይሳተፋሉ፡፡

በልምምዱ ከ50,000 በላይ ወታደሮች እና ከ5,000 በላይ የጦር መሳሪያዎች የሚያካትት ሲሆን 140 አውሮፕላኖች እና 60 የጦር መርከቦች, ጀልባዎች እና የድጋፍ መርከቦች በልምምዱ ይሳተፋሉ፡፡

ቮስቶክ-2022 የሚካሄደው እ.ኤ.አ በ1996 ሩሲያ፣ ካዛክስታን፣ ኪርጊስታን፣ ታጂኪስታን እና ቻይና በወታደራዊ ዘርፍ ያላቸውን በራስ መተማመን ለማሳደግ በገቡት ስምምነት መሰረት ነው፡፡
ANN

በቴሌግራም ይከተሉኝ
https://t.me/SuleimanAbdellaNews14

ሱሌማን አብደላ