Get Mystery Box with random crypto!

ሃቢብ ዑመር ሺአዎችን እርቃናቸውን ሲያስቀሩ ** አህለል በይቶች በአሏህ ትእዛዝ ላይ በመፅናት | ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

ሃቢብ ዑመር ሺአዎችን እርቃናቸውን ሲያስቀሩ
**

አህለል በይቶች በአሏህ ትእዛዝ ላይ በመፅናት ፣ እውነኞች በመሆን ፣ መልካም ባህሪን ፣ አስራርን በመወራረስ ነው ያሳለፋት ፣ አህለል በይትን በመውደድ ስም ማንንም መሳደብ ፣ አሳንሶ መመልከት ፣ መበደል ፣ በሙስሊሞች መካከል ፊትናን መቀስቀስ እንዲሁም ጥላቻ መዝራትን አያውቁም ።

* አህለል በይቶች የኢማናዊ ወንድማማችነት ፣ በአሏህ መንገድ የመዋደድ ምሽጎች ናቸው

* የቅኖቹ መንገድ ስለሆነው ስለ ሰሃቦች ፣ ታቢዒዮች እንዲሁም ንፁህ ስለሆኑ የአህለል በይቶች መንገድ ሰምታችኋል ፣ ይህን ጥላቻ ፣ ቂም ፣  ፊትና መቀስቀስ ፣ ወገንተኝነት በጭራሽ አያውቁትም ።

* እነርሱ ላይ መጥፎ ለሰሩ ሰዎች መልካምን ውለዋል ፣ እነርሱን የጎዳቸውን ሳይቀር ካለበት ስህተት ለማዳን ሰርተዋል ፣ የአሏህ ሰላትና ሰላም በሁሉም ላይ ይሁን።

የሃቢብ ኡመር ንግግር አበቃ

ስለ አህለል በይት ከአህለል በይቶች ስማ ፣ በሰሃቦች ጥላቻ ልቡ ከታወረ ፣ ቁርአንና ሃዲስን እንዳሻው ከሚጠመዝዝ ዋሾ ራስህንም ወዳጅ ዘመድህንም ጠብቅ ።

https://t.me/sufiyahlesuna