Get Mystery Box with random crypto!

አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ ~~~ ሱመያዊያን የበጎ አድራጎት ማህበር ለመቋቋም ከታቀ | ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ
~~~

ሱመያዊያን የበጎ አድራጎት ማህበር ለመቋቋም ከታቀደ ጥቂት ወራት አልፈውታል። ሀሳቡ በብዙ ሰው ዘንድ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ማህበሩን የመሰረቱት አባል ሸይኽ ሰዒድ ሁሰይን የሱመያ መስጂድ ኢማም እና ኸጢብ ማረፋቸውን ተከትሎ እያንዳንዱ የሚሰራው የኸይር ስራ አጅር ለእርሳቸው ይደርስ ዘንድ በማለት ቀድመው ጀምረውታል።

ማህበሩ የሚያተኮሩ በመሻይኾች ላይ ነው። የዑለሞቻችንን ወርቃማ የቀደመ ወደ ነብዩ ሙሐመድ የተሰላሰለ ሰነድ እስከ ቂያማ ድረስ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ ዒልሞቻቸውን ፣ አውራዶቻቸውን ፣ ኪታቦቻቸውን እና ታሪኮቻቸውን ለማጥናት ብሎም በሀያት እያሉ ነዳማ ሳይመጣብን በፊት በሙሉ አቅም ለማገዝ እና ከጎናቸው ለመቆም የታቀደ አላማ ነድፎ ተነስቷል።

በአሁኑ ወቅት በጥቂት የመሻይኾች አፍቃሪ እና ወዳጅ በሆኑ ወጣት አባላት የተዋቀረ ሲሆን ስራው በስፋት ተደራሽ እንዲሆን እና ብዙ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርቶ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሀይማኖቱ እና በመሻይኾቹ ዙሪያ የነቃ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ይቻል ዘንድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አባል ያስፈልገዋል። ለዚህም ውድ ወንድም እና እህቶቻችን የመሻይኾችን መንገድ ለማስጠበቅ እና ለማስቀጠል ፣ መሻይኾቻችንን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መንገድ እየደገፍን እና ታሪኮቻቸውን ለህዝብ እያስተዋወቅን ቀጣዩን ትውልድ ከአሁኑ እንቅረፅ።

ማንኛውም መሻይኾቼን እወዳለሁ ፣ ኢልማቸውን ማወቅ እፈልጋለሁ ፣ አውራድ እና ጦሪቃቸውን አስጠብቃለሁ የሚል ሰው የማህበሩ አባል መሆን ይችላል። ለአባልነቱ የተዘጋጀውን ፎርም በውስጥ መስመር

Telegram
ፈይሰል አብዱ(@Sumaliyano)
አብዱልሀኪም ናስር(@Hakiku01)
ኻሊድ አዳነ(@MERUEM222)
Facebook
ፈይሰል አብዱ
ጅብሪል አባስ (ibnu abas)
ኻሊድ አዳነ (azzrael azel)

በማነጋገር መሙላት ትችላላቹህ። ዝርዝር መረጃ ካስገለገ በስልክ ቁጥር

09 56 15 58 06 ኻሊድ አዳነ
09 11 26 55 62 ፈይሰል አብዱ
09 34 44 80 08 ራህመት ረዲ
በtelegeram channel
https://t.me/sumeya_charity_1
በ facebook ፔጅ ያግኙን
https://www.facebook.com/101233259389613/posts/pfbid0JsqseG2TJkRL66LVMA4qmLRoz28LZiyB8WwDw1eybndcZD3TbCcGgtdXGXovG5kXl/?app=fbl

በመሻይኾች መንገድ ህያው!
የሱመያዊያን በጎ አድራጎት ማህበር