Get Mystery Box with random crypto!

የጆሮ ደግፍ የጆሮ ደግፍ በመምፕስ ቫይረስ (Mumps virus) ምክንያት የሚከሰት ኢንፌክሽን ሲ | St. Urael Internal Medicine Clinic

የጆሮ ደግፍ

የጆሮ ደግፍ በመምፕስ ቫይረስ (Mumps virus) ምክንያት የሚከሰት ኢንፌክሽን ሲሆን በዋነኝነት ለጆሮያችን ቅርብ የሆነዉን የምራቅ ዕጢዎች የሚያጠቃ ነዉ። የጆሮ ደግፍ አንዱን ወይም ሁለቱን የምራቅ ዕጢዎች በብዛት ያጠቃል ። የጆሮ ደግፍ በወረርሽን መልክ ሊከሰት ይችላል። ወረርሽኑ በአጠቃላይ ያልተከተቡ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን፣ እንደ ትምህርት ቤቶች ፣ የኮሌጅና ካምፓሶች ባሉ ሰዎች የቅርብ ግንኙነት ያላቸዉ ቦታዎች በብዛት ይከሰታል።

የህመም ምልክቶች

አንዳንድ በመምፕስ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ወይ ምንም የህመም ምልክቶች ላይኖራቸዉ ይችላል አሊያም ምልክቶች ካሳዩ ቀለል ያለ ሊሆን ይችላል። የህመም ምልክቶቹ የሚከሰተዉ( የሚታየዉ) ለቫይረሱ ከተጋለጡ ከሁለት ወይም ሶስት ሳምንታት በኋላ ነዉ።

የጆሮ ደግፍ ዋነኛዉ የህመም ምልክት የምራቅ ዕጢዎችን በማሳበጥ ከጆሮ ማንጠልጠያ በታች ያለዉ የጊንጫችን ክፍል ህመም ያለዉ የጉንጭ ማበጥ እንዲከሰት ያደርጋል። ሌሎች የህመም ምልክቶች

· በአንዱ ወይም በሁለቱም በኩል ባሉ ባበጡ ምራቅ ዕጢዎች ላይ ህመም መኖር
· ትኩሳት
· የራስ ምታት
· የጡንቻ ላይ ህመም
· መደካከም
· የምግብ ፍላጎት መቀነስ ናቸዉ።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!