Get Mystery Box with random crypto!

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ ውስብስብና አጓጊ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው። ፕሬዚዳንት ጌ | Stalin Gebreselassie

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ ውስብስብና አጓጊ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው። ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል ባለስልጣናት ወደ አውሮፓ ያመራሉ እየተባለ ነው። ምናልባትም ዛሬ።

ኤርትራ እባክሽን ወደ ሀገራችን ግቢ እና ትግራይን በመጨፍጨፍ አግዢን ብለው የለመኑ እነ ታጋይ እስክንድር ነጋ ወደ ኤርትራ በረሃ ተሻግሮ ለኢትዮጵያውያን የትግል ችቦ አብስሯል።

ትግራይ የገባችው ኤርትራ በበኩሏ አዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ኤርትራ የደርግን ስርዓት ጥርሱን ሰባብራ ከ30 ዓመት በኋላ አስመራ የገባችበት እለት ተጋሩና ትግራይን በማጥላላት እንዲሁም ኢትዮጵያን ማሸነፏን በሚገልፁ ሙዚቃዎች አክብራለች።

ሚሊኒየም አዳራሽ ለትግራይ ልጃገረዶች የአሸንዳ በዓል ተከልክሎ፣ የካቲት 11 በዓል ጭምር ተከልክሎ ነበር ከጦርነቱ በፊት ጭምር።

አሪፍ ነው። ኢትዮጵያ በጥሩ ሀዲድ ላይ እየተጓዘች ይመስላል። አቀላጥፉት። ፍጠኑ።