Get Mystery Box with random crypto!

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ተልእኮ ከግብ ለማድረስ ቀዳሚ ተግባሩ አ | Stalin Gebreselassie

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ተልእኮ ከግብ ለማድረስ ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ እየሰራ መሆኑን የድርጅቱ ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ገለፁ።

በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ድርጅታቸው የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ተልእኮ ከግብ ለማድረስ ቀዳሚ ተግበሩ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ብኋላ በሁለቱም ወገኖች በርካታ ሰራዎች መሰራታቸውን እና ለውጦች መኖራቸውን ያነሱት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል በተለይም ከግዝያዊ አስተዳደር መመስረቱ ብኋላ ከፌደራል መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት መሻሻል እና ሌሎች በጎ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።

በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት ያልተፈፀሙ ትልልቅ ጉዳዮች ኣሉ።አሁንም ድረስ የትግራይ ግዛት በወረራ ይዘው በህዝባችን ላይ ጄኖሳይድ እየፈፀሙ ያሉትን የአማራ ታጣቂዎች እና የኤርትራ ሰራዊት መውጣት አልቻሉም። የተፈናቀሉን ህዝባችንም ወደ ቀየው ሊመለስ አልቻልም፣ ይህ ባስቸኳይ መተግበር ያለበት ጉዳይ ነው ብለዋል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ ማብራርያ የሰጡት የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ውሳኔው፣ የፕሪቶርያ ስምምነት የሚያፈርስ ተቀባይነት የሌለው ውሳኔ መሆኑን በማንሳት ደርጅቱ ሆነ የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ተቃውማቸውን መግለፃቸው እና ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቃቸውን ገልፀዋል።