Get Mystery Box with random crypto!

ሷሊሆች ለሷሊሆች ብቻ ናቸው ሀቢብና رسول صلى الله عليه وسلم

የቴሌግራም ቻናል አርማ solihmiset — ሷሊሆች ለሷሊሆች ብቻ ናቸው ሀቢብና رسول صلى الله عليه وسلم
የቴሌግራም ቻናል አርማ solihmiset — ሷሊሆች ለሷሊሆች ብቻ ናቸው ሀቢብና رسول صلى الله عليه وسلم
የሰርጥ አድራሻ: @solihmiset
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.03K
የሰርጥ መግለጫ

መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው፡፡እነዚያ(መጥፎዎቹ) ከሚሉት ነገር ንጹሕ የተደረጉ ናቸው፡ለእነርሱ ምህረትና መልካም ሲሳይ አላቸው
#ሌሎች_ቻናል_ይቀላቀላሉ
@RAHALE_qlebek
@Ye_setoch_jemaa_bech
#አስተያየት_መስጫ 👇
@solihmist_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-01 19:08:20 ‏عاجل:

*ነገ #ቅዳሜ የረመዳን የመጀመሪያው ቀን ነው።*

ነገ ፆም ይጀመራል ፁመው ከሚጨረሱት ያድረገን ኢባዳቸውን ከተቀበላቸው ባሮቹ ያድረገን

‏رؤية هلال شهر رمضان في سدير..
‏وغداً السبت أول أيام رمضان بالسعودية
.https://t.me/Muslimstudentsgroup
1.0K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 21:47:35 ለሙስሊሟ እህቴ

ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን -حَــفظهُ الله- እንዲህ ይላሉ:-

►ሙስሊሟ ሆይ ልብ በይ!

➧ሒጃብ እኮ መርዛማ ከሆኑ እይታዎች ይጠብቅሻል
➧ ከበሽተኛ ልብ እና ከሰው ውሾች የመነጨ እይታ ይከላከልልሻል

-➧የአሳዳጆችን ክጀላ ካንቺ ላይ ይቆርጣል

ስለዚህ ሒጃብሽ እንዳይለይሽ
ለአዘናጊዎች ጥሪ ጆሮሽን አትስጪ
ሒጃብን የሚዋጉ የሆኑትን ጥሪ (አትስሚ)
ወይም ጉዳዩን የሚያቃልሉትን ጥሪ (አትስሚ)
እነሱ ላንቺ መጥፎን ይፈልጉልሻልና!!

አላህ እንዲህ እንዳለው:-

﴿ وَيُرِيدُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الشَّهَوَاتِ أَنْ تَمِيلُوا مَيْلًا عَظِيمًا ﴾ .“

﴾እነዚያ ስሜታቸውን የሚከተሉት ደግሞ ከባድ የሆነን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ! ﴿
ተንቢሃት
፞ ፞
t.me/Ye_setoch_jemaa_bech

@Ye_setoch_jemaa_bech
1.3K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 19:06:32 ሽቶም ይሁን ዶዶራንት ወይም ሌላም የፈለግከውን ያህል ብትቀባው ቆይቶ ሽታው መጥፋቱ አይቀሬ ነው።
ፈፅሞ የማይጠፋ መዐዛ ያለው ሽቶ ግን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ!?

"መልካም ስነ—ምግባር ነው።"

(እኔ የተላኩት መልካም ስነ ምግባርን ለማሟላት ነው።)
(ረሱል ﷺ)
1.1K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 19:06:24 #በልጆች መካከል የሚከሰት ጠብ የልጆች የባህሪ ችግሮች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ነው

የሰው ልጅ በአጠቃላይ ልጅም ሆነ አዋቂ በብቸኝነት መኖር የማይችልና ማህበራዊነትም መገለጫው የሆነ ፍጡር ነው፡፡ ነገር ግን የበርካቶች መሰባሰብና አብሮነት ለተለያዩ የውድድር መንፈሶች መዳረጉ የታወቀ እውነታ ነው ከዚያም አልፎ ክርክር ፣አለመግባባት፣ንትርክና በአጠቃላይ የመልካም ግንኙነት መበላሸት መከሰቱ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፡፡ የዚህ ጉዳይ መሰረታዊ መነሻው ደግሞ በሰዎች መካከል ያለና የሚኖረው የሃሳብ፣ የፍላጎት (ዝንባሌ)፣የአስተዳደግ፤ የጥቅም፣ነገሮችን የምንመለከትበት መነፅር መለያየት ነው፡፡ አንድ ግልፅ መርህ ቢኖር እያንዳንዱ ግለሰብ ለሌላ ግለሰብ ሌላ ሰው የመሆኑ ሚስጥር ነው፡፡ እናም ያ ሰው በዚህኛው ላይ የተለያዩ ምቾቶችን የሚነፍጉ ድርጊቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈፀምበት ይችላል፡፡ ስለሆነም የማናችንም ቤት ከመጎናተልና ከመጎሻሸም እንደምን ሊወገድ ይችላል። ከላይ የጠቀስናቸው የተለያየ ስብዕና የተበላሱ ሰዎች በአንድ ጣራ ስር ሲኖሩ መነካካት የሚጠበቅ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የተለመደና ከቁጥጥር ውጭ የማይሆነው ንትርክና ከተለመደው ወጣ የሚል እንዲሁም አሳሳቢና አደገኛ የሆነም አይነት አለ፡፡

#በርካታ ጥናቶች እንዳመላከቱት በወንድማማቾች (እህትማማቾች) መካከል የሚኖር እሰጥ አገባ ከእድሜ መጨመር ጋር እየቀነሰ የሚመጣ ክስተት ነው ለምሳሌ የ 8 ዓመት ህፃናት (ልጆች) ከ 4 ዓመት ህፃናት ያነሰ ጠብ ውስጥ የመግባት አጋጣሚ አላቸው፡፡

በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል ፀበኝነቱ እንደሚበረታም ምሁራኑ አመላክተዋል፡፡
ተቀራራቢ እድሜ ባላቸው ለምሳሌ 5 እና 6 ወይ ከ1 ዓመት ወይም ከዓመት ተኩል እስከ 2 ዓመት ልዩነት ባለበት ትግሉ ይበረታል።
እዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባው ነጥብ ግን የትናንሽ ልጆች ጠብና ግብግብ ውስጥ የተወሰኑ ፋይዳዎች ያሉት መሆኑን ነው፡፡

እነዚህ ፋይዳዎች ምን ምን ናቸው የሚለውን በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን በአላህ ፍቃድ
949 views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 21:32:30 Watch "ውብ ቲላዋ ቁረአን የልብ ብረሃን سورة مريم city Saudi Arabia Jeddah" on YouTube


964 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 15:11:44
ሷሊሂ ቤተሰቦች የሷሊህ ልጆች መፍለቂያ ዋሻ ናቸው ።

➾ አባትና ልጅ አብረው ጉዞ እያደረጉ
➴ አባት ልጃቸውን ልጄ ሆይ !!እረምጃህን አስተካክል አሉት ።
➶ልጅም አባቴ ሆይ ! አንት እረምጃህን አስተካክል እኔ የምከተለው የአንተን እረምጃ ነው ። በማለት መለሰላቸው ።

#ቤተሰቦች ሷሊሂ ሲሆኑ ልጆችም የቤተሰቡን አረአያ ይከተላሉ።

https://t.me/solihmiset
╭─┅─═┅❀┅═─┅─╮             
  @Ye_setoch_jemaa_bech
@Ye_setoch_jemaa_bech
╰─┅─═┅❀┅═─┅─
#ሸር____share
1.0K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 22:14:07 ግንኙነት ያልተፈፀመበት ኒካሕ
~ ~ ~~~~
አንድ ሰው አንዲትን ሴት ኒካሕ አድርጎ ካገባ በኋላ ነገር ግን በመሃላቸው ግንኙነት ሳይፈፀም ከፈታት ፤ ለምሳሌ የተለያየ ሃገር እየኖሩ ኒካሕ ከታሰረ በኋላ ሳይገናኙ ፍቺ ቢፈፅም ዒዳ የለባትም። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና፦
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا إِذَا نَكَحْتُمُ الْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِنْ قَبْلِ أَنْ تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمْ عَلَيْهِنَّ مِنْ عِدَّةٍ تَعْتَدُّونَهَا فَمَتِّعُوهُنَّ وَسَرِّحُوهُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኳቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሯት ዒዳ ምንም የላችሁም፡፡ አጣቅሟቸውም፤ (ጉርሻ ስጧቸው)፡፡ መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው፡፡} [አል አሕዛብ፡ 49]
* ይሄ ጉዳይ የዑለማእ ኢጅማዕ ያለበት ነው።

ማሳሰቢያ፦

* ዳግም ማግባት ከፈለገ መስፈርቱን ያሟላ አዲስ ኒካሕ ማሰር እንጂ እንዲሁ መልሻለሁ ብሎ መመለስ አይችልም።
* ለመመለስ ሌላ አግብታ መፈታቷ ሸርጥ አይደለም። ሌላ አግብታ የተፈታች ባይሆንም ማግባት ይችላል። ነገር ግን የባለፈው ፍቺ አንድ ተብሎ ይቆጠራል። ስለዚህ ሁለት ኒካሕ ነው የሚቀረው ማለት ነው።
.
በፍቺ ሳይሆን በሞት ከተለየ ግን የዒዳው ብይን ይለያል። ማለትም ኒካሕ ታስሮ ግንኙነት ሳይፈፀም በፊት ባል ከሞተ አራት ወር ከ 10 ቀን ዒዳ ትቆጥራለች። ከንብረቱም ትወርሳለች። ሙሉ መህሯንም ትወስዳለች። የመህሯ መጠን ቀድሞ ያልተወሰነ ከሆነ የአምሳያዎቿ መህር ታሰቦ ይሰጣታል።
=
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
1.1K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 20:00:31
من صمت نجا
ዝም ያለ ነጃ ወጣ
ዝም አይነቅዝም
ጥሩ መልክ ነው

https://chat.whatsapp.com/JvmrGlrvw9m9b7WAmba0Tz
1.4K viewsedited  17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 08:38:12 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

#ዋና_ዋና_የህጻናት_የባህሪ_ችግሮች!

=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=

ውሸት

ሕጻናት ከሚገጥማቸው ችግሮች መካከል ዋናውና የመጀመሪው ውሸት ነው፡በአሁኑ ሰዐት ውሸት ከህፃናት አልፎ በአዋቂዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ይህ የሚሆነው የሰው ልጆች ለዱንያ ያላቸው ጉጉትና ፍቅር ድንበር ሲያልፍ፤ የማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል መብዛት፤ በተለይም የድህነት መስፋፋትና የእለት ጉርስን ማግኘት ሲከብድ ውሸታሞችን መብዛት ብንጠብቅ አይገርምም፡እናም አንድ ህብረተሰብ እውነተኛና ትክክለኛ ስልጣኔ ለመገንባት ከፈለገ ከእውነተኛነትና ውሸታምነት ጋር ያለውን ቁርኝት ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

#ውሸት_ምንድን_ነው?

አብዛኛውን ጊዜ ውሸት የሚፈጠረው ከሆነ ወንጀል(ስህተት) ወይም ማድረግ ያለብንን ስላላደረግን ወይም የሆነ ነውርን ለመደበቅ ሲባል ነው፡፡ ይህም ማለት አንድ ሰው በፈለገው መንገድ ይሁን የሚሰራውን ሰርቶ ለመደበቅ የሚችልበትና ለሰራው ስህተት የእጁን እንዳያገኝ የሚያስቸል ግርዶ ነው፡፡እናም ውሸት ላይ መዘውተር ማለት ለሁሉም መጥፎ ስራዎች በር መክፈት እንደሆነ ይታመናል፡፡

ስለህጻናት ውሸት ስናወራ ደግሞ ልጆች አንድ ከተከሰተ ነገር በተቃራኒ ሲናገሩ ዋሹ ብለን እንላለን:: ያም እውነታውን ለመደበቅ አልያም ሌሎችን ለማሳሳት ብለው የሚናገሩት ንግግር ሲኖር ነው፡፡

#የውሸት_አደገኛነት!

በማታለልና በውሸት እንዲሁም ቅጥፈት መካከል ጠንካራ ትስስር አለ፡፡ ዛሬ በአለማችን በሚከሰቱ ወንጀሎች ዙሪያ የተደረጉ በርካታ ጥናቶች እንዳመለከቱት ውሸታሞች በአብዛኛው ሌቦችና አታላዮች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ውሸት እንደባህሪ ያለበት ሰው ማታለልና መስረቅም አብረውት የሚገኙት ባህሪያቶቹ ናቸው፡፡ እናም ይህ ጥምረት የሚገርም አይሆንም ፡ ምክንያቱም ከሃዲዎች እውነታን፤ መርህንና ቃልኪዳንን ጭምር የሚክዱ ሰዎችን ካየን ይህ ባህሪያቸው የተፈለቀቀው ከውሸታምነታቸው መሆኑን እንረዳለን፡፡

ከዚህ በመነሳት የአላህ መልእክተኛ በቃልም በተግባርም ውሸትን አጥበቀው የመታገላቸውን ሚስጥር እንረዳለን። ይህን ያደረጉት በህጻናትም በአዋቂዎችም ላይ ነበር። አብደላህ ኢብኑ አማር የሚባል ሰሃባ እንዳወራው አንድ ቀን እናቱ ጠራችውና የሆነ ነገር እሰጣሃለው አለችው፣ ነቢዩም ምንድን ልትሰጪው ነው ሲሉ እሷም ቴምር አለች፣ እሳቸውም ምንም ባትሰጪው ይህቺው ንግግርሽ ውሸት ተብላ ትመዘገብብሽ ነበር አሏት፡፡

አኢሻም (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዓ.ወ) ከቤተሰባቸው በአንዱ ላይ ውሸትን ካዩበት ያ ሰው አምኖ ተውበት እስኪያደርግ ድረስ አያናግሩትም ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ የሚያሳየን ግልጽ አቋማቸውን ነው። ውሸት ካለበት ሰው ጋር ንክኪ የላቸውም በተግባርም በኩርፊያና በመለያየት በዚያ ሰው ባህሪም ላይ ያላቸውን ግልጽ ቅሬታ በማሳየት ዳግም ወደዚህ መጥፎ ስነምግባር እንዳይመለስ በተግባር ያስተምሩ ነበር። ይህም አሳዳጊዎችና ወላጆች ልብ ሊሉት የሚገባ መልካም አርአያነት ነው፡፡

#ህጻናት_ለምን_ይዋሻሉ?

በመጀመሪያ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ውሸት እዚህ አለም ከመጣን በኃላ በትምህርት፤ ከሌሎች በማየትና ከህይወት ተሞክሮዎች የምናገኘው ማህበራዊ ክህሎት እንጅ በተፈጥሮ የሚወራረስ ባህሪ አለመሆኑን ነው፡፡በአንድ ቤተሰብ አባላት ውስጥ የውሸት መስፋፋት የሚጠቁመው እዚያ ቤት ወይም ማህረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ዝቅተኝነትና ዋጋ ቢስነት ነው።

በአዎንታዊ መልኩ ህጻናት በሁለት መሰረታዊ ሁኔታዎች ለውሸት ተጋልጠው ልናገኛቸው እንችላለን፦

የቋንቋ አቅማቸው፡-
የልጆች የቋንቋ አቅም የሚፈቅደውን የቃላት ብዛት በመጠቀም የሚፈልጉትን ነገር ሊናገሩ ይችላሉ። ይህም ፍላጎታቸው ከእውነታው ጋር ምን ያህል ይጣጣማል የሚል እሳቤን ላያካትት ይችላል፡፡

የምናብ ግጥምጥሞሽ መከሰት፡-
ሁኔታወችን በራሳቸው ምናብ በማገጣጠም እውነት ያልሆነን ነገር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡
ነገር ግን በአሉታዊ አንፃር ስናየው ህጻናትን ወደ ውሸት የሚገፋፉ ዋና ዋና ምክንያቶችን እናያለን፡

1. ቅጣትን በመፍራትና የምፈልገውን ነገር እከለከላለሁ በሚል ፍርሃት መዋሸት

2. ወላጆችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን ለማሳመንና ያጠፉትን ጥፋት እንዲቀበሉት ለማስገደድ ጉልበትንና ቅጣትን በተገበሩት ቁጥር ልጆች እራሳቸውን ለማዳን ሲሉ መዋሸት

3. በአድማጮቻቸው ለመደነቅ ወይም ትኩረትን ለመሳብ

4. የሆነን ነገር ለማግኘት ብሎ መዋሸት (ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲሉ ከትምህርት ቤት አምጡ ተብለናል በማለት ገንዘብ መቀበል ሊሆን ይችላል)

5. ከራሳቸው ላይ አደጋን ለመከላከል ሲሉ እርስ በርስ ሊውሻሹ ይችላሉ

6. ከወላጆች በመቅዳት የነሱን ባህሪ መያዝ፡- የሚዋሹ ህጻናት ብዙውን ጊዜ የሚዋሹ አባቶቻቸውን ወይም እናት ወይም ታላላቅ እህትና ወንድሞቻቸውን ኮፒ አድርገው እናገኛቸዋለን፡ አንድ ወጣት ይህን አስመልክቶ ሲናገር አባቴ ሲሰራና ሲናገር የማየው ነገር በሙሉ ትክክልና እውነት ይመስለኝ ነበር፡ ውሸትን የተማርኩት ከአባቴና እናቴ ነው፡፡በአንድ ወቅት እኔ እንድተኛ ብለው እነሱ እንደተኙ ያስመስላሉ ከዚያ ስተኛ ተነስተው የሚሄዱበት ይሄዳሉ አንዴ እናቴ እንዲህ አለችኝ ይላል ተነስ መጫወቻ ቦታ ልውሰድህ ብላ በጣም ደስ ብሎኝ እየሄድን ስንደርስ እራሴን የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ወንበር ላይ አገኘሁት ይላል፡፡

=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=

በቀጣይ ልጆቻችን ላይ ውሸትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን የሚለውን እናያለን በአላህ ፍቃድ፡፡

Join our telegram channel
https://t.me/+16kPTqOEQUwxM2I0
1.1K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 22:06:17 ኢማሙ ራዚ እንዲህ ይላሉ፦
ቀደም ሲል ከነበሩ አሊሞች አንዱ በርካታ ተማሪዎች ነበሯቸው። ከተማሪዎቻቸው ውስጥ ግን አንዱን የበለጠ ይወዱትና ያቀርቡት ነበር። ተማሪዎቻቸውም ለምን እሱን ከሌሎቻችን አብልጠው እንደሚወዱትና እንደሚያቀርቡት ጠየቋቸው። ኡስታዙም ምክንያቱን ለማወቅ ከፈለጋችሁ ጠብቁ ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ አንድ ዶሮ ሰጥተው አላህ ከማያያቹህ ስፍራ ሄዳችሁ ዕረዱና አምጡ አሏቸው። ሁሉም ተማሪዎች በየ አቅጣጫው ተሰማርተው የተሰጣቸውን ዶሮ አርደው መጡ። ያ ተማሪ ግን ዶሮዋን ሳትታረድ ከነ ነፍሷ ይዟት ተመለሰ።
ኡስታዙም፦ ምነው ሳታርዳት ከነ ነፍሷ ይዘሃት መጣህሳ ብለው ጠየቁት። ተማሪውም እርስዎ አላህ ከማያይህ ቦታ አርደህ ና አሉኝ አላህ የማያየኝን ቦታ ግን ማግኘት አልቻልኩምና ነው ይዤ የተመለስኩት አላቸው።
የዚህን ግዜ ኡስታዙ ለዚህ ስል ነው ከሁላችሁም በተለየ መኘኘልኩ የምወደውና የማቀርበው ሲሉ መልስ ሰጧቸው።

እርስዎ ከዚህ ቂሳ ምን ተማርን!?


የተከነዘባችሁትን ኮሜት መስጫው ላይ ፆፉልንን

https://t.me/Muslimstudentsgroup
911 viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ