Get Mystery Box with random crypto!

ቅድስት ፌብሮኒያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ slehiwetwe — ቅድስት ፌብሮኒያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ slehiwetwe — ቅድስት ፌብሮኒያ
የሰርጥ አድራሻ: @slehiwetwe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ስለ ሕይወታችን የምንወያይበት ሁላችንም ሀሳብና አስተያየት የምናካፍልበት ነው ፤ እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ይለቀቁበታል።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-03 20:30:11 እንኳን ወደ ፍኖተ ወንጌል የቴሌ ግራም ቻናላችን በሰላም መጡ። ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዶግማ ቅኖና ሥርዓት መሰረት ያደረጉ ትምህርቶች በድምጽ ይተላለፉበታል።


ፍኖተ ወንጌል
https://t.me/terwahdo
182 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 17:19:09 ሰንበትን አክብር

በመምህር አቤል
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
295 views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 16:12:14 ቅዱስ
በዘማሪ ይትባረክ።
298 views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 09:42:02 የተወደደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-

እግዚአብሔርን የምትወዱት፥ ይልቁንም እግዚአብሔር አብልጦ የሚወዳችሁ ሆይ!

ሕፃናት የእናታቸውን ጡት ለመጥባት ምን ያህል እንደሚጓጉ አስተውላችኋልን? እኛም ወደ ቅዱሱ ማዕድ መቅረብ ያለብን፣ ከመንፈሳዊው ጽዋ ጡትም ለመጠጣት መጓጓት ያለብን እንደዚህ ነው፡፡

ሕፃናቱ የእናታቸውን ጡት ሲያዩ እንዴት ደስ እንደሚሰኙም ተመልክታችኋል! እኛም የመንፈስ ቅዱስን ፍቅር ስንመለከት ደስ ሊለን የሚገባው እንደዚህ ነው፡፡

ሕፃናቱ የእናታቸው ጡት ሲከለከሉ ምርር ብለው እንደሚያለቅሱ ኹሉ፥ እኛም ከዚህ ማዕድ (ከቅዱስ ቁርባን) ስንርቅ ምርር ብለን ልናለቅስ ይገባናል::
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
459 views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 16:23:25 ከቅዱሱ ስፍራ ከቤተክርስቲያን በቅዳሴው፣ በትምህርቱ፣ ሚስጥራቱን ሁላ ተሳትፋችሁም ሆነ የግል ጸሎት አድርጋችሁ እንዲሁ በጎ ነገር ሰርታችሁ ስትጨርሱ ውስጣችሁን የደስታ፣ የእረፍት፣ የተስፋ፣ አንዳች ስሜት በውስጣችሁ ከተሰማችሁ እርሱ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አስተውሉ።
አባታችን አቡነ ሽኖዳ
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
446 views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 10:46:18
ወንድሜ አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ። ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል። የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ አባ ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም "ከመከራ መራቅ የሚወድ ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል። በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ። በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3

አባታችን አቡነ ሽኖዳ
577 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 08:28:59
ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ማንንም አላገኝም ፣ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላሰተውል ደካማ ነኝና ፣ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ። ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፊኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን ብቼኝነት አይሰማኝም ። ያለ አንተ ግን ባዶነቴ ያስጨንቀኛል ። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል።ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳልኝ ከቶ የለም ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ
629 views05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 08:38:29
አለመፀለይ ትዕቢት ነው።

@slehiwetwe ይቀላቀሉን።
828 viewsedited  05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 20:27:21 ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን
ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት
ትወድቃለህ።
# በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።
# ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
# ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል!
# ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
# ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
# ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ
፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው
ትገፋበታለህ።
# ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
# ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣
ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል።
# እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ
ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።
በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው
ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
መስገድ ያቅትሃል።
መጾም ይከብድሃል።
ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
# ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
# በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ
ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ
ነበር።
# ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ
ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች
ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
# የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣
የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሄር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።።
959 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 10:06:13
ሙሉ ገቢው ለደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ እድሳት የሚውል #የግዮን_ወንዝ የሚል አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን ከሙሽራው ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ለገበያ ይቀርባል።
487 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ