Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ! ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ | Skyline media

ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረቧን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ በመግለጫቸውም ኢትዮጵያ ጥቅሞቿን ሊያስጠብቁ ከሚችሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገልጿል።

"ብሪክስ ከኢትዮጵያ ለቀረበለት ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ እንደሚሰጠን እንጠብቃለን።" ያሉት አምባሳደር መለስ፤ ከሌሎች ብሔራዊ ጥቅሞችን ሊያስጠብቁ ከሚችሉ ተቋማት ጋር መስራታችንን እንቀጥላለንም ብለዋል።

አባል አገራት ያቀረቡትን የእንቀላቀል ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጥ ተገልጿል።ሳውዲ አረቢያ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ ግብጽ እና አልጀሪያ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ ካቀረቡ አገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።