Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ሁሉን አቀፍ ትብብር እና አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስ | Skyline media

የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ሁሉን አቀፍ ትብብር እና አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ወቅታዊ ግንኙነት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫውም በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች እና በድርቅ ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ክፉኛ መጎዳታቸውን እና የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ተፅዕኖ ውስጥ መውደቁን አንስቷል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ የተከሰቱ ችግሮችን ለመቋቋም የዓለም ባንክ ቡድን ከኢትዮጵያ ያለውን ሁሉን አቀፍ ትብብር እና አጋርነት እንደሚያስቀጥል ነው ያስታወቀው፡፡
ባንኩ ባለፉት አስርት አመታት በተደረጉ ሰው ተኮር ድጋፎች በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን እና አሁን ላይም ባንኩ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች መሰረታዊ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሷል፡፡
በመላ አገሪቱ ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ያለው የባንኩ መግለጫ ÷በሀገሪቱ የሰላም ግንባታን፣ እርቅን እና ዘላቂ ሰላምን የሚያበረታቱ ጅምሮችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጿል።