Get Mystery Box with random crypto!

በበጀት አመቱ 9 ወራት ምንም አይነት ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ከውጭ የልማት አጋሮች እንዳልፈሰሰ የገ | Skyline media

በበጀት አመቱ 9 ወራት ምንም አይነት ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ከውጭ የልማት አጋሮች እንዳልፈሰሰ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በበጀት አመቱ 7.7 ቢሊየን ብር ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ እንደሚኖር ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ምንም አለመገኘቱን ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ያስታወቁት፡፡

ከሰሜኑ ግጭት ጋር ተያይዞ አጋር አገራት እና ተቋማት በተለይ ምእራባውያን መንግስት ላይ ጫና ለማሳረፍ በማሰብ ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ በአብዛኛው ማቀዛቀዛቸው ይታወሳል፡፡
በመሆኑም መንግስት ከአጋሮች ለወትሮው ሲያገኘው የነበረው ድጋፍ ባለፉት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ ቅናሽ ታይቶበታል፡፡