Get Mystery Box with random crypto!

አትላንታ የጆርጂያ ስቴት ዋና ከተማ ስትሆን እነ አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ኃይሌ ገብረስላሴ በአትላ | Skyline media

አትላንታ የጆርጂያ ስቴት ዋና ከተማ ስትሆን እነ አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ኃይሌ ገብረስላሴ በአትላንታ ኦሎምፒክ ታሪክ የሰሩበት ከተማ ነው።

ከተማው በአለም ስም ጥር ገናና እና የአለምን አይዲኦሎጂ በሚያሾሩ እጅግ ገናና ጋዜጠኞች መገኛም ያሉበት ሲኤልኤን ዋና መቀመጫ እንዲሁም የኮካ ኮላ መጣጥ መገኛ በመሆን ይታወቃል።

ስመጥሩው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተርም መፍለቂያቸው ጆርጂያ ነው። የአውሮፕላን አብራሪዎች ትምህርት ቤትም በአለም ስመ ጥር ፓይለቶችን እያስመረቀ የሚያወጣ ልዩ ማሰልጠኛም አላቸው።

ወደ አትላንታ ሰማይ ቀና ብለው ሲመለከቱ በርካታ አውሮፕላኖችን አየር ላይ ሲያዥብቡ ሊመለከቱ ይችላሉ ምክንያቱም ማሰልጠኛው እዛው ነው። በኒዮርክ መንታ ህንጻዎችን በ9/11 የነበረውን አደጋ ያደረሱት ወጣት ፓይለቶችም የዚሁ ማሰልጠኛ ምሩቃን እንደነበሩ እናስታውሳለን።

የኢትዮጵያውያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ በቀጥታ ወደ አትላንታ መብረሩ አትላንታንም ሆነ የጆርጂያ አጎራባቾችን በቀጥታ ከአፍሪካ የማገናኘት አቅም አለው።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤም የአትላንታውን አቻቸውን በሲኒ ቡና ቺርስ ሲሉ ታይተዋል። በተለይ አዲስ አበባ ከአትላንታ ATL ብዙ መማር ትችላለች። አዲስ አበባም እንደ አትላንታ የራሱ የሆነ ልዩ ስጦታ ለአለም ያለው መሆኑን ማስመስከርና ሰርታ ማሳየት ይኖርባታል።

ከንቲባ አዳነች አጋጣሚውን በመጠቀም ለከንቲባው ያደረጉት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አዲስ አባ አዲሳባ የሚሸይ ቆንጆ አቀበባበል ነውና ልናመሰግናቸው ይገባል።