Get Mystery Box with random crypto!

#Oromia የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ባካሄደው  መደበኛ  ጉባኤው የተለያዩ | Skyline media

#Oromia

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ባካሄደው  መደበኛ  ጉባኤው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ውሳኔዎቹ ምድናቸው ?

ውሳኔዎቹ ከከተሞች አደረጃጀት ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለትና ከዛ በላይ ከተሞችን አንድ ላይ እንዲደራጁ ተወስኗል።

1. ቢሾፍ ከተማ ፦ የቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እንዲሁም የመዘጋጃ ቤት ከተሞች ሂዲ፣ ኡዴ ደንካካ እና ድሬ በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ10 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

2. ሻሸመኔ ከተማ፦ የሻሸመኔ ከተማ እና የብሻን ጉራቻ ከተማ በመቀላቀል በ4 ክ/ከተሞች እና በ12 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

3. አዳማ ከተማ፦ የአዳማ ከተማ እና የወንጂ ከተማን በመቀላቀል በ6 ክ/ከተሞች እና በ19 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

4. ሮቤ ከተማ፦ የሮቤ ከተማ እና የጎባ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

5. ማያ ከተማ፦ የሀረማያ ከተማ፣ የአወዳይ ከተማ እና የአዴሌ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

6. ባቱ ከተማ፦ የባቱ ከተማ እና የአዳሚ ቱሉ ከተማን በመቀላቀል በ7 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሚከተሉት ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ተወስኗል፡፡

1. መቱ ከተማ
2. አጋሮ ከተማ
3. ቡሌ ሆራ ከተማ
4. ነጆ ከተማ
5. ሰንዳፋ በኬ ከተማ
6. ሸኖ ከተማ
7. ሞያሌ ከተማ
8. ዶዶላ ከተማ
9. ሻክሶ ከተማ

ከዚህ ባለፈ የሚከተሉት ከተሞ ደረጃ እንደሚከተለው እንዲሻሻል ተወስኗል።

1. አዳማ፣ ሻሻመኔና ቢሾፍቱ ከተሞች፡- የሬጂዮ-ፖሊስ ከተማ

2. የሮቤ ከተማና የማያ ከተማ፡- ዋና ከተማ

3. የመቱ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌና ሻክሶ ከተማ፣- ወደ ከፍተኛ ከተማነት እንዲያድጉ ተወስኗል።

በሌላ በኩል የምስራቅ ቦረና ዞን አዲስ ዞን ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል፡፡

በአዲስ መልክ 21ኛ ዞን ሆኖ የተደራጀው የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና ከተማው ነጌሌ ቦረና ሆኖ፡-
• ከቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ፣ ሞያሌ ከተማ፣ ጉቺ ወረዳ እና ዋችሌ ወረዳ፣
• ከጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ፣ ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ፣ ነጌሌ ቦረና ከተማ፣
• እንዲሁም ከባሌ ዞን መደወላቡ ወረዳ፣ ኦቦርሶ ወረዳ እና ሀረና ቡሉቅ ወረዳ በመጨመር እንደ ዞን 10 ወረዳዎችን በመያዝ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

በአዲሱ አደረጃጀት የምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጂ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል።

የመደ ወላቡ ወረዳ ደግሞ በሁለት ቦታ ማለትም የመደ ወላቡ ወረዳና ኦቦርሶ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅና የጭናክሰን ወረዳ የነበረው በሁለት ወረዳ የጭናክሰን ወረዳና የመከኒሳ ኦሮሞ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል።