Get Mystery Box with random crypto!

የ4ኛዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የንግድ ቤት ጨረታ ነገ ጥር 3/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2 | Skyline media

የ4ኛዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የንግድ ቤት ጨረታ ነገ ጥር 3/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሰንጠረዡ ውስጥ በተጠቀሱት የመሸጫ ፕሮጀክቶች / ቦታዎች የሚጀመር መሆኑን የአ/አ ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን አስታወቀ።


በ40/60 ፕሮግራም በተለያዩ ክ/ከተሞች ያስገነባቸውን 5,397 በጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚፈልግ ዛሬ አሳውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጥር 3/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 6/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ባሉት 28 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በአካል በመቅረብና የማይመለስ ብር 400 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

የት ነው የጨረታው ሰንድ የሚገዛው ?

- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ
- ሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች ብሎክ 4
- የካ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ
- የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 4ኛ ፎቅ
- 40/60 ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት
- 40/60 አያት 49 ማዞርያ ብሎክ 21 ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት

የጨረታ ሳጥን የካቲት 6/2015 ከቀኑ 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ የካቲት7/2015 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራጮች በተገኙበት ይከፈታል ተብሏል።