Get Mystery Box with random crypto!

የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር | Skyline media

የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል።

ከተማ አስተዳደሩ በ14 ኛ ዙር የ2080 የቤት ልማት ፕሮግራም 18 ሺ 930 ቤቶች፣ በ40/60 ደግሞ 6 ሺ 843 ቤቶች እንዲሁም ተጨማሪ 18 ስቱዲዮ ቤቶች በድምሩ 25 ሺ 791 ቤቶችን እጣ የማውጣት መርሃ ግብር በማካሄዱ የሚዘነጋ አይደለም።

ውል የመዋዋያ ቦታው #መገናኛ በሚገኝው የቦሌ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ