Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ታሪክ ስነዳ ሂደት ሞጋቹ ፕሮፌሰር - ዶ/ር  ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ ************* | Skyline media

በኢትዮጵያ ታሪክ ስነዳ ሂደት ሞጋቹ ፕሮፌሰር - ዶ/ር  ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ
**********************

ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ በቀድሞው በከንባታ እና ሐዲያ አውራጃ በኩፋላ ሐበሌ ግንቦት 12 ቀን 1930 ዓ.ም ተወልደው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቢቾ ሆሣዕና ሚሽን ት/ቤት እና በመንግሥት ትምህርት ቤት ሲከታተሉ ቆይተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አዳማ በሚገኘው በአጼ ገላውዴዎስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ባይብል አካዳሚ  ተምረዋል።

ከዚያም ወደ አሜሪካ በማቅናት በኮሙኒቲ ኮሌጅ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለው በኀብረተሰብ ታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲም በአፍሪካ ታሪክ ጥናት የማስትሬት ዲግሪያቸውን፣ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እና በአውሮፖ ታሪክና በፍልስፍና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል።

ዶክትሬታቸውን ካጠናቀቁ  በኋላ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸው ለሁለት ዓመታት በቨርጂኒያ ዩንየን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተው አብዮቱ ሲፈነዳ ‘የታሪክ አካል መሆን አለብኝ’ በማለት ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። ያኔ የነበራቸውን ስሜት ሲገልፁ “የኢትዮጵያ አንድነትን እንደ ጣኦት እያመለኩት መጣሁ” ይላሉ።

በአሜሪካን ሀገር በፍልስፍና እና በታሪክ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ሲማሩ ከአምስት መቶ ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት ከፍተኛ አድናቆት ማትረፍ ችለዋል። በዚህም ምክንያት  በርካታ የአሜሪካን ሀገር ዩንቨርስቲዎች የነፃ የትምህርት ዕድል በአማራጭነት አቅርበውላቸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0QqMHTvURLqukvcR74zi4ZorPLC42NQjBFu2oY7drke8vKetEVU2n8bBKc3tnW1Htl