Get Mystery Box with random crypto!

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ******************* አርቲስት ማዲ | Skyline media

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*******************

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው አርቲስቱ ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ሕክምና ማድረጉንና ከቆይታ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም ለተጨማሪ ምርመራ አስከሬኑ ወደ ሆስፒታል መላኩንም ለማወቅ ተችሏል።