Get Mystery Box with random crypto!

ወሳኝ የጥንቃቄ መልዕክት ሼር! ሼር! ይሄንን መረጃ ያገኘሁት ከማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ከጁንታው | Skyline media

ወሳኝ የጥንቃቄ መልዕክት ሼር! ሼር!

ይሄንን መረጃ ያገኘሁት ከማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ከጁንታው ደጋፊዎች ዘንድ ውስጥ ውስጡን ሲዘዋወር ነው።
ሃገር ቤት ያላችሁ የሰራዊትን እንቅስቃሴ ከመጠቆም መቆጠብ አለባችሁ።
እኔ ያየሁት መረጃ ይሄንን ይመስላል።

{"ጥብቅ መረጃ!!

ምሽቱን ከባባድ የጭነት መኪናዎች፣ ሜካናይዝድ የጦር መሣሪያዎችን የጫኑ ተሳቢዎች እና ተደጋጋሚ የአየር በረራዎችን በመጠቀም የብልጽግና መንግሥት ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ኮማንዶ ተዋጊ ኃይል ከአዲስ አበባና ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ አካባቢ ሲያንቀሳቅስ ማደሩን ከውስጥ ምንጮች ማወቅ ተችሏል።

የዐቢይ ሠራዊት ይህን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ ኃይልና የጦር መሣሪያ ወደ ምስራቅ ግንባሮች ማለትም ወደ ዓፋር ማስገባቱ በቀጣይ በዚህ ግንባር መጠነ ሰፊ ዘመቻ ለመጀመር ያለውን ዕቅድ የሚያሳይ ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ቀናት ውስጥም ወደ ኦፕሬሽን ሊገባ እንደሚችል ምንጮቻችን ገልፀዋል።"}
እንዲህ አይነት ሚስጥር ማውጣት ለጠላት መረጃ እንደመላክ ይቆጠራል። እንጠንቀቅ። የሰራዊቱን እንቅስቃሴ ከመግለጽ እንቆጠብ።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=112805584881597&id=107429748752514