Get Mystery Box with random crypto!

በጉጉት ስጠበቅ የነበረዉ 'ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ' የተሰኘው የታሪክ መጻሐፍ ምረቃ ፕሮግራም | Skyline media

በጉጉት ስጠበቅ የነበረዉ "ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ" የተሰኘው የታሪክ መጻሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ይፋ ሆነ

መጽሐፉ በአማርኛ ቋንቋ ስለዎላይታ ህዝብ ታሪክና በኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ላይ ህዝቡ ስላበረከተው አስተዋፅኦ የሚያትት ስሆን መስከረም 7/2015 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ አዲስ አበባ 4ኪሎ በሚገኘዉ አብሮሆት ህዝብ በተመጻህፍት አዳራሽ ይመረቃል።

የታሪኩ ጸሐፊ አማኑኤል አብርሃም ባባንቶ እጅግ ባማረ አጻጻፍ እንደከተበዉ ታላላቅ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን አስቀምጠዋል።

ፀሐፊው ከዚህ ቀደምም "የመረጃ ነፃነት በኢትዮጵያ" በሚለው መጽሐፉ በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ በምን መልኩ መጠናከር እንዳለበት የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።

በጋዜጠኝነት፣ በፖለቲካ አመራርነት አሁን ደግሞ በዲፕሎማሲው ረገድ ያካበተውን ልምድ ተጠቅሞ ታሪካችንን የሚያድስ ገፀ በረከት ይዞ ብቅ ብሏል።

ከመጽሐፉ ሽያጭ ለአካባቢው ልማት ቃል የገባ መሆኑ እጅግ የሚያስመሰግን ለሌሎች ደራሲያን መልካም አርአያ እና በር የከፈተ በመሆኑ ክብር አለን!!!

መጽሐፉ በወልማ አማካኝነት በሁሉም ቅርንጫፍ ባለባቸው አከባቢ የሚሸጥ ስለሆነ በፖስተሩ ባለው ስልኮች ደዉለዉ መግዛትና ማንበብ ይቻላል።

ገዝተው እንዲያነቡት ለወዳጅ ዘመድም እንዲያጋሩት ተጋብዘዋል!
መልካም ንባብ

ታሪክ ሳይዛባ ከትቦ ማለፍ ለዛ ማህበረሰብ ቀጣይነት ወሳኝ ነው! !