Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአንጎላ ጠቅላላ ምርጫ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ የአፍሪካ ህብረት | Skyline media

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአንጎላ ጠቅላላ ምርጫ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን የሚመሩት የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአንጎላ ጠቅላላ ምርጫ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅድመ ምርጫ ውይይታቸው የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ ከተለያዩ ምርጫ አስፈጻሚ አካላት ጋር መክረዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የአንጎላ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ማኑኤል ዳ ሲልቫንም ማነጋገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአንጎላ ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ረቡዕ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡