Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ በደረሰ የህንፃ መናድ ' እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን | Skyline media

በአዲስ አበባ በደረሰ የህንፃ መናድ " እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ህንፃው የተደረመሰው በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዪ ቦታው መሃል አዳራሽ በሚባል አካባቢ አንድ አሮጌ ህንፃ በመናዱ ምክንያት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ 6 ሰው የሞተ ሲሆን ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ላይም ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል::

ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እና ያስከተለውን ጉዳት እያጣራ ይገኛል ስል አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።