Get Mystery Box with random crypto!

በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሠላም | Skyline media

በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሠላም ተገላገለች።

ወ/ሮ ታምራት ታፈሰ ትባላለች ከድል በገሬራ ነው የመጣችው። ከዚህ በፊት መንታ ሴቶችን በሠላም እንደተገላገለች ተናግራለች።

በዩኒቨርስቲው ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማህፀንና ጽንስ ት/ት ክፍል የመጨረሻ ዓመት ተማሪ የሆኑት ዶክተር አንተነህ ቼሩ እንደገለጹት ፤ ወ/ሮ ታምራት የጽንስ ክትትል በኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማድረጋቸውንና በወሊድ ወቅት በተደረገላቸው እርዳታ ሦስት ወንድ ልጆችን በሠላም መገላገሏን ተናግረዋል።

እናትም ሆነ ሕፃናት በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙም ዶክተር አንተነህ ገልጸዋል።

እናት በበኩላቸው በተቋሙ ባለሙያዎች በተደረገላቸው ዕርዳታ አመስፐነዋል ስል የኮሌጁ ኮ/ሕ/ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የ WT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/