Get Mystery Box with random crypto!

“መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ | Skyline media

“መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው”፦ የዓለም የምግብ ፕሮግራም
**

የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ እያደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያደንቁ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዳቪድ ቢስሌይ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዳቪድ ቢስሌይ እና የስዊድን ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ማቲልዳ ኤርንክራንስን በዛሬው ዕለት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የስዊድን ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ማቲልዳ ኤርንክራንስም የኢትዮጵያ መንግሥት ለዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

በውይይቱ በግጭት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ስለሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ፣ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከተካሄደው ጦርነት ጋር ተያይዞ ስለሚነሱ የግልጽነት ጉዳዮች እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የጋራ መተማመንን በመፍጠር ረገድ እየወሰዳቸው ስላሉ እርምጃዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል።

የ WT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/