Get Mystery Box with random crypto!

Sime Tech

የቴሌግራም ቻናል አርማ simetube — Sime Tech S
የቴሌግራም ቻናል አርማ simetube — Sime Tech
የሰርጥ አድራሻ: @simetube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 932
የሰርጥ መግለጫ

በቻናሉ ውስጥ
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች
📢 ተወዳጅ አፖች
📢 የሶፍትዌር ትሪኮች
📢 የwebsite ጥቆማዎች
📢 የኮምፒውተር ትምህርቶች
📢 የሳተላይት ዲሽ መረጃ
📢 በቪዲዮየተደገፉ
📢የTech መረጃዎችንና
📢ሌሎች ትምህርቶችን በስፋትና በጥራት
ያገኛሉ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-07 04:48:17
በአለም ላይ እስካሁን ከተሰሩት የሞባይል ስልኮች በትልቅነት አቻ ያልተገኘለት በ #ክሪኬትና በ #ሳምሰንግ ድርጅቶች የተፈበረከው Samsung Model SCH-r450 ነው::
ይህ የሞባይል ስልክ የተሰራው በፈረጆቹ 2009 ሲሆን የሚገኘውም በምድረ አሜሪካ ቺካጎ ነው በተጨማሪም SCH-t450 የተባለው ትልቁ ሞባይል (15 ጫማ ርዝመት) : (13 ጫማ ከፍታ) እና (3 ጫማ ጥልቀት) በጋራ ይዟል

ይህ ግዙፍ ሞባይል ለእይታ ሲቀርብ ለጎብኝዎች የማያቋርጥ የድምፅ እና የመልክት አገልግሎት ይሰጥ ነበር...
- ከአለምም ትልቁ ሞባይል በመባልም በጊነስ ወርልድ ሪኮርድሰ መዝገብ ላይ ሰፍሯል።

@simetube
548 viewsedited  01:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-27 15:58:04
ይህንን ሊንክ ይጫኑት&Share

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

https://telegram.me/learnGeez1
https://telegram.me/learnGeez1

Join ያድርጉና የግእዝ ቋንቋን ይማሩ!!!!

@learnGeezbot

ለአስተያየት ይጠቀሙ
704 views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-22 20:44:28 የስልካችን ሚሞሪ ምድነዉ የሞላዉ?
መፍትሄዉስ?
***********
***********
የአብዛኞቻችን የራስምታት የሆነብን በስልካችን ላይ ቪድዮ ሙዚቃ አፕልኬሽን ስንጭን ሙሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage avaliable) የሚለዉን pop up dialog እንዴት ሚሞሪያችን #free አድርገን አንደምናስተካክል እናያለን።

ግን ለምን ይመጣል?

የ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስራ(አፕልኬሽን install ለማድረግ ፋይል ለማስቀመጥ ...) የመስራያ ቦታ ሲያጣ ይከንን #Notification ያሳየናል።

የአንድሮይድ አፕልኬሽኖች ማስቀመጫ storage አይነት ይጠቀማሉ።

ለ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት #memory አለ።

ለራሳቸዉ ለ አፕልኬሽኑ #data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት #memory አለ።

ለአፕልኬሽኑ #catch ጊዜያዊ ፋይል ማስቀመጫ #memory አለ።

እነዚህ #Catch ላይ የተቀመጡ ፋይሎች ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።

መፍትሄ

ቆይ መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።

የስልካችሁ ለማየት #Internal storage ምን ምን እንደሞላዉ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ ።

#Setting ዉስጥ ይግቡ

ከዛ #Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።

አዚህጋ የ RAM,Internal Storage,SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።

Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።

Avaliable :አሁን ያላችሁ #free የሆነ የሚሞሪ መጠን ነወ።

System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እግደ Setting,Chrome,Phone,GMail,Google,Contacts,Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት #memory ያሳየናል።

Owners እኛ የጫናቸዉን አፕሌኬሽኖች, ፎቶዎች,ያሳየናል።
አዉድዮ ፋይሎች እና Catch ሚሞሪ ላይ ያሉት ፋይሎች የያዙትን የሚሞሪ መጠን ያሳየናል።

አሁ ከላይ ካየሐችሁት ዉስጥ ብዉ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።

አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን #uninstall ማድረግ።

uninstall ለማድረግ #Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።

ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።

Video ከሆነ የማትፈልጉትን #Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።

Audio ከሆነም አሸዛዉ ምረጡና አጠያጥፉ

የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ እና እንደ Other#Screenshot የመሣሠሉትን ፋይሎች ያጥፉ

Clear data የሚለዉን በመጫን #catch ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ

ሌላኛዉ አማራጭ ትላልቅ ፋይሎችን ከ Internal Memory ላይ #Cut አድርጎ ወደ SD card ላይ ፔስት ማድረግ ነዉ።

ሌላዉ አማራጭ SD Card የስልኩ defalu ፍይል (Apps,photo,video,audio በቂ ሁሉንም ነገር)
ማስቀመጫ ማድረግ ነዉ።

ይከን ለማድረግ

Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናተ SD card የሚለዉን ይምረጡ።

muhammed computer technology
ስልኩ እየሞላበት የተቸገረ ጓደኛችሁ ስለሚኖር #Share አድርጉላቸዉ።
═════❁✿❁ ═══════

@simetube @simetube
779 viewsedited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-22 19:43:36
_________________________________
እውነተኛ ሁለ ገብ መረጃዎችን በማስተላለፋቸው ብቻ ተከታያቸው ነኝ ፤ እናም ሁሌ ስለ ሀሰተኛ ቻናሎች ብቻ ከምነግራቹህ በሚል ይህንን ተዓማኒ ቻናል ለማስተዋወቅ ወደድኩ ።
________________________________


#ስለ_ወቅታዊ የግቢዎች ሁኔታም ይዘግባሉ


#እውነተኞችን ማስተዋወቅ #መልካም ተግባር ነው ብዬ አምናለሁ።
576 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 21:51:28
ማይክሮሶፍት ቀጣዩ ዊንዶውስ ዊንዶውስ 11 ተብሎ ሊጠራ የሚችል ሰኔ 17 ቀን ሊገለጥ ነው ፡፡ የሶፍትዌሩ ግዙፍ ኩባንያ ቀደም ሲል እንደገለጸው ዊንዶውስ 10 በዓለም ላይ በሁሉም ስፍራ የሚገኝ ኦፕሬቲንግ ሲስተም “የመጨረሻው ስሪት” እንደሚሆን ቀደም ሲል ገልፁዐል፡፡ ኩባንያው ሀሳቡን እንደለወጠ የሚጠቁሙ ፍንጮች

የማይክሮሶፍት ዋና ምርት ኦፊሰር ፓኖስ ፓናይ በእነማው ላይ ቁጥር 11 ላይ ፍንጭ የሚሰጥ ፍንጭ በትዊተር ላይ ለጥፎ የነበረ ሲሆን ማይክሮሶፍት አዲስ የዊንዶውስ 11 ጅምር ድምፅን የሚያሾፍ የ 11 ደቂቃ ቪዲዮ በዩቲዩብ ላይ በቅርቡ አሰራጭቷል።

@simetube

@simetube ||
@simetube ||

▬▬▬▬▬▬ sʜᴀʀᴇ ▬▬▬▬▬▬
584 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 17:14:00 ስልክዎ #ቀርፋፋ እየሆነ ተቸግረዋል?

. የስልክዎ Internal Storage ሲሞላ

ፋይል ይቀንሱ፤ ትልልቅ ፋይሎችን ወደ Sd Card #Move ያድርጉ።

. ስልክዎ ውስጥ #Virus ሲገባ

. ከራሱ ከስልኩ ሌላ #launcher ሲጠቀሙ

የራሱን #Launcher ይጠቀሙ።

. የያዙት ስልክ #Original ካልሆነ

ስልኩ #ኮፒ ከሆነ መንቀራፈፉ ወይም ስታክ ማድረጉ ማይቀር ነው።

. ተጨማሪ

መጀመሪያ #Setting ውስጥ ትገባላችሁ በመቀጠል *developer option ውስጥ ትገባላችሁ አንዳንድ ስልኮች ላይ developer option በቀጥታ ስለማናገኘው *about phone ውስጥ ገብተን build number የሚለየውን ደጋግመን ስንነካው developer option ይመጣልናል በመቀጠልም *window animation scale, transition animation scale & animation duration scale 3ቱንም #Off እናደርጋቸዋለን።

@simetube @simetube
534 viewsedited  14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 17:02:40
አዲስ ተለቀቀ የተባለው window 11 ይሄን ይመስላል።

@simetube @simetube
@simetube @simetube
475 views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 16:54:11 በስልካችን ቪዲዮዎችን በማቀናበር ፕሮፊሽናል ኤዲተር መሆንእንዴት እንችላለን?
ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም! ዘመን አፈራሽ የሆነው ስልክዎ ከኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮዎችን ለማቀናበር አንዲያደርጉ ያስችሎታል!

ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 8 አፖች እነሆ!

1ኛ፦ FilmoraGo
በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የAndroid ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው! የመቁረጥ (Trim/Cut) ገጽታዎችን መቀየር፣ሙዚቃን ወዘተ... የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ በዚህ መተግበሪያ ሊያከናወኑ ይችላሉ!

2ኛ፦ VideoShow
ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ አስደናቂ መተግበሪያ ሲሆን PlayStore ውስጥ ከሚገኙ ነፃ ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው! ለአጠቃቀም ቀላል ነው! ከዋና ዋና ተግባራቶቹ ውስጥ ፊልተሮችን፣ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም በቀጥታ ስርጭት ጊዜ ቪዲዮዎን መቆጣጠር፣ማስዋብ ይችላሉ!

3ኛ፦ PowerDirector
ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ገራሚ የቪዲዮ ኤዲተር ነው! በቸኮሉ ጊዜ አልያም ፈጣን ግዜያዊ (ቋሚ) ቪዲዮዎችን በሰአታት ውስጥ ለመስራት ግሩም የሆነ አማራጭ ነው!

4ኛ፦ KineMaster
ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነ-ገጽ ጋር በመጣመር #KineMaster ለAndroid ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው! የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ ❝Copy Paste❞ አገልግሎትን መጠቀም ይችላሉ! ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር የKineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ተመራጭ ነው! የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን (ብሎግ) ማስገባት ይችላሉ! ብቻ ይሄ መተግበሪያ የግድ ስልክዎ ላይ ሊኖር ይገባል! የኤዲቲንግ ፍላጎት ካላችሁ!

5ኛ፦ Quik
እጅግ በጣም ገራሚ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ሌላው ብልጥ መንገድ ነው! ፈጣን እና ነፃ ነው። የራሳችሁን ታሪክ በQuik ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ! ሌላው #ለQuik ይተውት! በጣም ጥሩው ነገር ደግሞ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎን ማሳደግ መቻሉ ነው! ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ውስጥ ቪዲዮዎችን #Crop ማድረግ፣ማሳመሪያዎችን፣ጽሑፎችን መጨመር እና ቪዲዮዎችን ከሙዚቃ ጋር ለማመሳሰል ፈጣን የሆነ አማራጭ ነው!
6ኛ፦ VivaVideo
ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት! መተግበሪያው በቀጥታ በስልክዎ ፕሮፌሽናል የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው! ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ! በውስጡ ዘገምተኛ (#SlowMotion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ስሪት እና የተንሸራታች ማሳያ #SlideshowMaker አለው!

7ኛ፦ FuniMate Video Editor
በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል! የዕለት ተዕለት ኑሮዎን በቀጥታ ወደ ፈጠራ ቪዲዮዎች ለመለወጥ እና የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት! አጭር ቪዲዮዎችን #ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ የላቁ አማራጮች አሉት!

8ኛ፦ Magisto
መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው! ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፎቶግራፎችን ሙዚቃን ጽሑፎችን (የቪዲዮ ውጤቶችን) እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል!

@simetube @simetube
@simetube @simetube
#join_us
507 views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 16:43:48 ውድ ወዳጆቻችን ዛሬ እነሆ አሪፍ የተባሉ የ #ቴሌግራም #ቦት ዎች ጋበዝናችሁ!

@utubebot - #ዩቲዩብ ላይ ያሉ ቪድዮዎች በቴሌግራም ማውርድ ከፈለጋቹ ይህን #ቦት ተጠቀሙ! ከናንተ ሚጠበቀው ልታወርዱት የፈለጋችሁት #የቪዲዮ ው ሊንክ ለቦቱ መላክ ብቻ ነው!
GoTo Official YouTube App -> Search You're Favorite Videos -> Click 3 Dot (፧) -> Share -> CopyLink Or Share To Telegram (utubebot).

@spotify_to_mp3_bot - በSpotifybot ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሙዚቃዎች ይገኛሉ! የምትወዱትን መርጣችሁ #Download አድርጉ!

@XompressorBot - ማንኛውም Mp3 ፎርማት ሳይዛቸው ለመቀነስ ይጠቅማል!

@pdfbot - ይህ ቦት የፈለጋቹትን #Pdf_File ለመስራት እና ለማንበብ የሚያስችል ነው!

@Uloadit_bot - ወደ ቴሌግራም #file #Upload ለማድረግ ይጠቅማል!

@ScreenShotTGBot - የፈለጋችሁት ማንኛውም አይነት #ቪዲዮ #Screenshots በማድረግ ይልካል! ፊልም ለምታወርዱ ደግሞ ይህ አሪፍ ማረጋገጫ ነው!

@GmailBot - #Gmail አፕ አያስፈልጋቹህም ይሄ ቦት አለ መልክት መላክ መቀበል የሚያስችል በGmail #Verify የሆነ ቦት ነው!

@silentcbot - ይህ #ቦት የቴሌግራም #ቻናል ላላቸው እና ከሁለት በላይ አድሚኖችን ለመቆጣጠር ይረዳል! ለምሳሌ አላስፈላጊ #ጹሁፍ #እስቲከር ወይም #ሊንክ እንዳይልኩ ያደርጋል!

@encoderbot - ይህ #ቦት ደግሞ #Telegram ላይ ልናወርዳቸው የፈለግናቸው #ኦዲዮዎች ብዙ #Mb በሚሆንብን ጊዜ ለመቀነስ ይረዳናል!
ማሳሰቢያ ይህ #ቦት በቀን ውስጥ ከ4 ወይም ከ5 በላይ #Audio #Convert ማድረግ አይችልም!

@MathCalcBot - የቴሌግራም #Calculator #ቦት ነው ይጠቅማቹሀል!

@GHAnnunciBot - ቻናል ላላችሁ ጠቃሚ የሆነ #ቦት ነው!

@NoteOfficialBot - ማስታወሻ ለመያዝ የሚጠቅም ምርጥ #ቦት ነው!

@virus_total_scan_bot - ፍይሎቻችንን #Scan በማድረግ ከቫይረስ ነፃ መሆናቸውና አለመሆናቸውን የሚነግር አሪፍ #ቦት ነው!

የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #UnMute በማድረግ የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ!
#join_us & #share
@simetube @simetube
@simetube @simetube
473 viewsedited  13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 16:39:53 ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን ላይ Sleep, Hibernate, Shutdown ልዩነታቸው ምንድን ነው?

ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ መንቀራፈፍ ይጀምራል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም ማሳረፍ ያስፈልጋል።

ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን። ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው። እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች በዝርዝር እንመለከታለን።

“ስሊፕ”

በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ” የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።

ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል። የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።

ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ። በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ ማድረግ ተገቢ ነው።

“ሸት ዳውን”
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም። በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም። ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር) ይወስዳል።

“ሀይበርኔት”

ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው። “ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ። ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥ ከ“ስሊፕ” አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው። በሀይበርኔትም ሆነ “ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው ሀይል ተመሳሳይ ነው።

ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።

መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?

በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም። ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።

ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።

ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን”ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ ይልቅ “ሀይበርኔት”ን ይመርጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን” ማድረጉ ተመራጭ ነው።

ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው። ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል። ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ። “ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል።በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል።

@simetube @simetube
ከወደዱት ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ
420 viewsedited  13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ