Get Mystery Box with random crypto!

የባል ሀቅ(መብት)፡- ኢስላም ሚስት በባሏ ላይ መብት እንዳላት ሁሉ ባልም በሚስቱ ላይ መብት እን | ትዳር የአማኞች ምሽግ

የባል ሀቅ(መብት)፡-

ኢስላም ሚስት በባሏ ላይ መብት እንዳላት ሁሉ ባልም በሚስቱ ላይ መብት እንዳለው ያስተምራል፡፡
ለዛሬ ባል በሚስት ላይ ያለውን መብት ይዘንላችኋል፡፡
የባል መብት ሚስት በሏን በማክበር፣ አለማሳጣትና አለመናቅ ይጠበቅባታል፡፡ አስተያየቱን ማጣጣል፣ ንግግሩን ያለምንም ምክንያት ውድቅ ማድረግ፣ በፍቅር ፈንታ ጥላቻን ማሳየት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡
ባል ሚስቱን የማዘዝ መብት አለው፤ እርሷም የመታዘዝ ግዴታ አለባት፡፡
ይህም ሲባል ግን የወንድ ትምክህተኛነትን እና አምባገነንነትን ኢስላም ይቀበላል ማለት አይደለም፡፡
ሚስት ባሏን አሚን ብላ የምትቀበለው ከተፈቀዱ(ሃላል)
ዘርፎች ውስጥ እስካልወጣ ድረስ ነው፡፡ በአንድ ቤት ውስጥ ሁለት መሪ ሊኖር አይችልምና መለኮታዊውን የስራ ድልድል በመቀበል ሚስት ለባሏ ትእዛዝና መልካም ፈቃዶች ታዛዥ ሆና መገኘት ይኖርባታል፡፡
ይህ ካልሆነ ቤተሰባዊ ሰላም አይገኝም፡፡ ሁለቱም ወገኖች አንድና ወጥ
የሆነ አመለካከትና ጎዳና መከተል ይሳናቸውና እየቅል ይሆናሉ፡፡ በመጨረሻም ወደተጠላው ፍች ያመራሉ፡፡

https://t.me/SileTidarEnmekaker