Get Mystery Box with random crypto!

'ህወሓት ዳግም ጦርነቱን የጀመረው ለጦርነቱ የሚያስፈልገውን ሀብት ከየት አግኝቶ ነው ' - ጋ | ሸገር jobs

"ህወሓት ዳግም ጦርነቱን የጀመረው ለጦርነቱ የሚያስፈልገውን ሀብት ከየት አግኝቶ ነው
" - ጋዜጠኛና ደራሲ አን ጋሪሰን

መሰረቷን በጀኔቫ ያደረገችው እና ለበርካታ መገናኛ ብዙኃን የምትሰራው አን ጋሪሰን የተሰኘች ጋዜጠኛ ህወሓት "ትግራይ ተከባለች፣ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይገባ ክልከላ ተደርጓል" የሚል ማደናገሪያ እያነሳ ባለበት ሰዓት፣ ጦርነቱን ዳግም ለመጀመር የሚያስችለውን ሀብት ከየት አግኝቶ ነው በሚል የተቃርኖ አመክንዮ በትዊተር ገጿ አንስታለች።

ጦርነት ውድ እና ያልተቋረጠ መሳሪያ፣ ተተኳሽ፣ ተሸከርካሪ፣ የምግብ አቅርቦት፣ የስለላ ቴክኖሎጂ እና ሌሎች አቅርቦቶች እንደሚፈልግ በመጥቀስ፣ "እነዚህ አስፈላጊ ግብዓቶችን ቡድኑ ከየት አገኛቸው?" ስትል ጥርጣሬ አዘል ጥያቄዋን አን ጋሪሰን አጋርታለች።

ትላንት አሸባሪው ህወሓት መቀሌ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ድርጅት መጋዘን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉንና የሰብአዊ እርዳታ ስርጭቱን መስራት ከማይችልበት ደረጃ መድረሱን ተመድ መግለፁ ይታወሳል።


#ArifNeger

#Ethiopia #Ethiopiannews #ዜና #News

ለፈጣን መረጃዎች
ዩትዩብ: https://youtube.com/c/Addisnegertop10

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@arifneger24

ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Arifneger

ቴሌግራም: https://t.me/arifnegermedia

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Arifnegermedia/

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!