Get Mystery Box with random crypto!

ቅዳሜ ጠዋት የወጡ ስፖርታዊ ዜናዎችን ማንችስተር ዩናይትዶች ቪኒሲየስ ጁኒየርን ለማዘዋወር እየተ | SPORT 360⚽️

ቅዳሜ ጠዋት የወጡ ስፖርታዊ ዜናዎችን

ማንችስተር ዩናይትዶች ቪኒሲየስ ጁኒየርን ለማዘዋወር እየተዘጋጁ ነው ዩናይትዶች ኮከቡን ይፈልጋሉ ተጨዋቹ በማድሪድ የቀረበለትን አዲስ ኮንትራት እስካሁን ለመፈረም ፍቃደኛ አደለም ቪኒሲየስ በፒኤስጂም ይፈለጋል(ElNacional)
.
ቸልሲዎች የተከላካያቸውን አንድሪያስ ክሪስተንሰንን ውል እንደሚያራዘም ተማምነዋል ቸልሲዎች ተጨዋቹ በአመቱ መጨረሻ እንዳይለቅ የተሻለ ኮንትራት አቅርበው ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት አላቸው(Footballinsider)
.
የአስቶንቪላው አዲሱ አሰልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ በጥር ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ሁለት ትላልቅ ዝውውሮችን ለመፈፀም ተዘጋጅቷል ጄራርድ ስማቸው ይፋ ባይደረግም ተከላካይ እና አማካይ ተጨዋች ለማስፈረም ተዘጋጅቷል(FootballInsider)
.
ጁቬንቱሶች ሜምፊስ ዴፓይን ለማስፈረም እየተመለከቱ ነው ተጨዋቹን ከዚህ በፊትም ለማስፈረም ይፈልጉ ነበር ባርሴሎናዎችም ለተጨዋቹ ሚመጡ ጥያቄዎችን ለመስማት ዝግጁ ናቸው(ElNacional)
.
ሪያል ማድሪዶች ኤርሊንግ ሀላንድ ዶርትመንድን መልቀቅ ካሰበ ሊያስፈርሙት ዝግጁ ናቸው ዶርትመንዶች ከተጨዋቹ ዝውውር እስከ €75m ይፈልጋሉ(GOAL)
.
ቶተንሀሞች የሮማውን ኮከብ ኒኮሎ ዛኒሎን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ተጨዋቹ ኮንትራቱ በ2024 ይጠናቀቃል ሆኖም እስካሁን ኮንትራት ለማራዘም ፍላጎት የለውም እናም የረጅም ጊዜ ፈላጊዎቹ ቶተንሀሞች ከሮማ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ናቸው(calcioMercato)
.
ላዚዮዎች የቸልሲውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋን በውሰት ለማዘዋወር ይፈልጋሉ ተጨዋቹ በቸልሲ ተጠባባቂ ግብ መሆንን አይፈልግም ስለሆነም በቸልሲ አብሮት ከሰራው ሳሪ ጋር በላዚዮ ለመገናኘት ይፈልጋል(calcioMercato)
.
ሊቨርፑሎች የዋትፎርዱን የመስመር አጥቂ ኢስማኢል ሳርን ለማስፈረም በድጋሚ ፍላጎት አሳይተዋል የ23 አመቱ ኮከብ ከዚህ በፊትም በሊቨርፑል ተፈልጎ ነበር ሳር በዋትፎርድ ደስተኛ ነኝ ብሎ ነበር ነገር ግን ሊቨርፑሎች በጥር ሊያመጡት ይፈልጋሉ ሳር በዋትፎርድ ሶስት አመት ኮንትራት አለው(calcioMercato)
.
ማንችስተር ሲቲዎች ስተርሊንግ ወደ ብቃቱ እንደሚመለስ ያምናሉ እናም አዲስ ኮንትራት እንዲፈርም ለማሳመን ይጥራሉ ስተርሊንግ በሲቲ 18 ኮንትራት ብቻ ይቀረዋል(theSun)
.
ናፖሊዎች ሁለቱን የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች የሆኑትን ማሪያኖ ዲያዝን እና ሉካ ጆቪችን ለማስፈረም ይፈልጋሉ ተጨዋቾቹ በማድሪድ ቤት አይፈለጉም ይህንንም ተከትሎ ሁሉቱም ተጨዋቾች ወደ ጣሊያን ሊያመሩ ይችላሉ(Fichajes)
.
ባርሴሎናዎች ኤዲሰን ካቫኒን በጥር የማስፈረም ፍላጎት የላቸውም የአጉዌሮን ከኳስ መራቅ ተከትሎ በሱ ምትክ አጥቂ ለማምጣት ሚገደዱት ባርሳዎች ሌላ አጥቂ በጥር ለማምጣት ይፈልጋሉ(elnacional)
.
የ26አመቱ ሚሊንኮቪች ሳቪች ፖል ፖግባን በመተካት ወደ ማንችስተር ሊያመራ ይችላል ማንችስተሮች ተጨዋቹ ላይ ፍላጎት ማሳየት ከጀመሩ አመታት የተቆጠሩ ሲሆን አሁን ላይ ፖግባን ለመተካት ተመራጭ ነው(CalcioMercato)
.
ኒውካስትሎች የማንችስተር ሲቲውን የመስመር ተከላካይ አሌክሳንደር ዚንቼንኮን በውሰት ለማስፈረም ይፈልጋሉ ተጨዋቹ በካንሴሎ ስር መሆኑ ተጨማሪ የመጫወቻ እድል ለማግኘት ቡድኑን በውሰት ሊለቅ ይችላል(DailyMail)( ማራኪ ስፖርት)
ታውቋል ።

https://t.me/dark2_sport https://t.me/dark2_sport