Get Mystery Box with random crypto!

የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ቀብር በኢትዮጵያ እንደሚፈጸም ተነገረ! በእሁድን በኢቢኤስ ፕሮግራም አዘጋ | Sheger Press️️

የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ቀብር በኢትዮጵያ እንደሚፈጸም ተነገረ!

በእሁድን በኢቢኤስ ፕሮግራም አዘጋጅነትና አቅራቢነት ተወዳጅነትን ያተረፈው አንጋፋው የራዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ አስከሬን ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ቤተሰቦቹ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት የሥንብት ሥነስርዓት እንደሚካሄድ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን አስታዉቋል፡፡

የፊታችን ሃሙስም ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሜሪላንድ በሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን የፍትሃት ሥርዓት እንደሚከናወንለትና ቅዳሜ ጥር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የአስከሬን ሽኝት ይደረግለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

በአዲስ አበባም በቀብር ሥነስርዓቱ አፈጻጸም ዙሪያ በአገር ውስጥ ኮሚቴ ተዋቅሮ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የቀብሩን ቀንና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በይፋ በሚሰጥ መግለጫ እንደሚነገር ኮሚቴው አሳውቋል።ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በህክምና ሲታገዝ ቆይቶ ለህክምና በሄደበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ለሊት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

[ዳጉ ጆርናል]
@sheger_press
@sheger_press