2022-10-05 20:54:31
ምዕራባውያን አይሸነፉም፣ አይቻሉም አትበሉን።
============
ምዕራባውያን የመጨረሻውን ሽንፈት ተሸንፈው የተሰበሩት አፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ ላይ ነው። ይሄንን ታሪክ ስነግረው ውሸት ነው የሚል ሰው አይጠፋም።
አዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት አደራሽ ውስጥ ሄዳችሁ መጠየቅና ተፅፎ የተቀመጠውን ታሪክ ማንበብ ትችላላችሁ።
ያሁኑ ትልውድ የነሱ አምላኪ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት የነበሩት አፍሪካዊያን ሳይማሩ በጥቁርነታቸው የሚኮሩ ናቸው። አሁን ላይ ነጭ የሰራው ልብስ መኪና፣ ጌጣጌጥ አባባል ሁሉም እውነት መስሎን እነሱን እንደፈጣሪ እናመልካለን። የአፍሪካ ፋሽን ልብስ ግን አለም ገበያ ላይ ቢወጣ ማንም ዞሮ የሚያየው የለም።
ነጮቹ ግን የአፍሪካን ማዕድን እየወሰዱ መልሰው አሳምረው ሲያስተዋውቁት እልል ብሎ የሚገዛ ባለስልጣናት ነው አፍሪካ ውስጥ ያለው።
የምዕራባውያን ሀሳብ ትክክል መስሎ የሚታየው መሪ አፍሪካ ውስጥ እስካለ ድረስ አፍሪካ ነፃ አትሆንም። ወርቅ ለምዕራባውያን ሰቶ ዶላር የሚበደር ጭንቅላት ያለው ሰው እንዴት ነው የአገሩን ኢኮኖሚ የሚቀይረው ? እንዴት ነው ከባርነት የሚላቀቀው።
እኔ ግን አንዲት የሊቢያ ወርቅ ለነሱ አልሰጥም። እዚሁ አገሬ ላይ የወርቅ ባንክ አስቀምጠዋለሁ እንጅ አንድም የሊቢያ ወርቅ ለነሱ አይሸጥም።
ፕሬዚዳንት መሀመድ ኡመር (ጋዳፊ) ከ14 አመት በፊት ፓርላማ ላይ ተናገረው የተወሰደ !
via ነጋሽ
992 views17:54