Get Mystery Box with random crypto!

ሰውነት 🗣🚶‍♀🚶‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ sewnet_et — ሰውነት 🗣🚶‍♀🚶‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ sewnet_et — ሰውነት 🗣🚶‍♀🚶‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @sewnet_et
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.94K
የሰርጥ መግለጫ

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፤ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል
☞የፍልስፍና ስራ ሰውን ለተፈጠረበት የሰውነትአላማ ማብቃት ነው
❖ጥንታዊ ፍልስፍናዎች
❖አስገራሚ አውነታዎች
❖ሳይኮሎጂ
❖አስደማሚ ታሪኮች
❖መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት
☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል
🗣 @JohnXv

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-07-27 00:38:43 "ከታሪክ የምንማረው ሰዎች ከሌሎች ታሪክ እንደማይማሩ ነው" ይለናል ጆርጅ ሄግል የተባለ ፈላስፋ። አየህ ትናንት መማሪያ እንጂ የቁጭት መወጫ አይደለም!

ግሩም ሰኞ ተመኘንላችሁ
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.9K viewsJohn ㋛︎, edited  21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-27 00:38:43 ድንቅ ልማድ

አንድ ልማድ ስትጀምረው እንደማይታይ ክር ነው፤ ያ ክር እርስበርሱ ሲደጋገም ሲጠላለፍ ትንሽ ቆይቶ በቀላሉ የማይበጠስ ሀያል ገመድ ይሆናል።

አየህ አሪፍ ልማድን ስትጀምረው እንደ ክሩ ስስ ነው፤ ለመበጠስ ቅርብ ነው፤ ስትደጋግመው ግን አንተ ውስጥ ጠንካራ ማንነት ይፈጥራል።

ግድ የለህም ወዳጄ በጠዋት መነሳቱን፣ ማንበቡን፣ ስፖርት መስራቱን፣ ቋንቋ መለማመዱን በቃ የጀመርከውን አሪፍ ልማድ ሳትሰለች ትንሽ ደጋግመው፤ ከዛ ምን አይነት ሰው እንሚያደርግህ ታየዋለህ!
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.8K viewsJohn ㋛︎, edited  21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-27 00:38:43 ራስን መቀየር

ለሰዎች መምከርማ እንችልበታለን! ምን ቢያደርጉ እንደሚሻል ከነሱ በላይ እኛ እናውቃለን፤ ችግሩ እሱ አይደለም "ለራሴስ እንዴት ልወቅበት?" ነው ጨዋታው።

አንድ የማከብረው ሰው "አገሬን እቀይራለው ብዬ ተነሳው ብዙም ሳልቆይ እንደማይሆን ገባኝ፣ አይ መቀየር ያለብኝ ከተማዬን ነው አልኩ እሱም እንደማይሳካ ሲገባኝ ሰፈሬን አልኩ፣ ከዛ ቤተሰቦቼን አልኩ....በመጨረሻ የገባኝ ነገር መጀመሪያ ራሴን መቀየር እንዳለብኝ ነው" ይለናል።

ጣፋጭ ምሽት ተመኘንላችሁ
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.7K viewsJohn ㋛︎, edited  21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-24 12:46:28 ታሪክህን የሚቀይረው ከፈጣሪ ቀጥሎ ያንተ ቆራጥነት ነው! ከሰዎች ብዙ አጠብቅ! ሰዎችን አንዳስቀመጥክ አታገኛቸውም ጊዜና ሁኔታ ይቀይራቸዋል። ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ማለት ስትጀምር በአመለካከት ከፍ ማለት ትጀምራለህ።

የሚያስደስት ቅዳሜ ተመኘንላችሁ
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.7K viewsJohn ㋛︎, edited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-24 12:46:28 ህይወት በቀላሉ የሚገመት ቢሆን አጓጊ መሆኑ ያቆም ነበር፤ ስለዚህ ለምን እንደምፈልገው አልሆነም ብለህ አትዘን...ግን የምትፈልገው ነገር እስኪፈጠር ድረስ ጥረትህን አታቁም ምክንያቱም የተሸነፍከው ያቆምክ ዕለት ነው!

@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.6K viewsJohn ㋛︎, edited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-24 12:46:28 ልብ በል!

አሁን ያለህበት ሁኔታ አንተን አይወስንህም ወይ አንቺን አይወስንም ፤ አሁን ያለህ ነገር የዛሬ አምስት አመት ጀምሮ ታስባቸው የነበሩ ታረጋቸው የነበሩ ነገሮች ውጤት ነው ።

አሁን በተደጋጋሚ የምታስበው ፣ የምትሰራው ፣ የምታደርገው ነገር ደግሞ ቀጣይ 5 ዓመትህን ይወስናል ስለዚህ በተደጋጋሚ ስለምታስበው ፣ ስለምትሰራው ፣ ስለምታደርገው ነገር ወስን !

ቆንጆ ከሰዓት ተመኘን
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.6K viewsJohn ㋛︎, edited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-24 12:46:28 ህልም!

ህይወት አሰልቺ የሚሆነው ጥልቅ መሻት እንቅልፍ የሚነሳ ህልም ከሌለህ ብቻ ነው!

ለደሞዝ ብቻ የምትሰሪ ወይ የምትሰራ ከሆነ የዛሬውን ቀን ለቀሪው ዘመንህ መደጋገም ግድ ነው፤ ደሞዝተኛ ከመሆን በላይ ትልቅ ፍላጎት ያስፈልግሀል!

ለመመረቅ የምትማር ከሆነ አታስብ ትመረቃለህ ያንተን ትንሽ ጥረት ነው የሚጠይቀው፤ ከመመረቅህ በላይ ራስህን የሚያስገርምህ ህልም ያስፈልግሀል!

ትዳር ነው የምትፈልጊው፤ አታስቢ እህቴ ታገቢያለሽ ግን ከዛ በላይ አስገራሚ ቤተሰብ የመፍጠር ህልም ያስፈልግሻል!

መቼ እንደምታሳኩት አላውቅም ህልሙ ካለ እንደምታሳኩት ግን አውቃለው!
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.5K viewsJohn ㋛︎, edited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-22 23:06:25 ወዳጄ 'አልችልም' ካልክ ልክ ነህ አዎ አትችልም፤ 'እችላለሁ'ም ካልክ ልክ ነህ አዎ ትችላለህ! ሁሉም በመዳፍህ ነው! ስለዚህ አይምሮህ ካመነበት እስኪ ንገረኝ የምትፈልገውን እንዳታገኝ የሚያስቆምህ ማነው?!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.6K viewsJohn ㋛︎, edited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-21 15:43:17 ስኬት

አሁን ካለህ በላይ ስኬት ከፈለግክ አሁን ካለህ በላይ ምን ለማድረግ ወስነሃል? ነው ጥያቄው ። የፈለግከውን ያሻህን መመኘት መፍትህ ምን ለማድረግስ ዝግጁ ነህ ?

አሁን ካለህ እጥፍ ከፈለግክ አሁን ካለክ እጥፍ ራስህን አዲስ ነገር ለመሞከር ፣ ለመሣሣት ክፍት አርግ !

ሰናይ ቀን ተመኘን
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.6K viewsJohn ㋛︎, 12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-21 12:02:24 ተዘጋጅ!

የመጣልህ ዕድል ትክክለኛ ነው ወይስ ካንተ የሚጠበቅ ተጨማሪ ዝግጅት አለ? ይሄን ለማወቅ መታገስ አለብህ፤ አየህ ስኬት ማለት ዝግጅት ሲደመር እድል ነው።

ካልተዘጋጀህ የሚመጣውን እድል እንዴት አርገህ ልትጠቀምበት ነው? ሳትሰለች ራስህ ላይ ስራ ነገሮች ሁኔታዎችና ዕድሎች አሳደው ይከተሉሀል።

ልዩ ረቡዕ ተመኘንላችሁ
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
1.4K viewsJohn ㋛︎, edited  09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ