Get Mystery Box with random crypto!

ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት ክፍል አስራ አምስት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት
ክፍል አስራ አምስት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ዬ ዬ ዬ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

"ለከ ሃይል"ን በል

ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ

ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ : ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ : ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል።

ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ : ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ) : አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ : እስከ አራት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ ፸፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ : እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ : ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ (በውርድ ንባብ) እያስገባ ያንብብ።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል

አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ 
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል

ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ : ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ : ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ።
ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮

ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ : ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ።

ማቴ: ፳፯ : ፵፮ - ፶ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ

ማር: ፲፭ :፴፬ - ፴፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።

ሉቃ: ፳፫ : ፵፭ - ፵፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ።

ዮሐ: ፲፱ : ፳፰ - ፴ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join