Get Mystery Box with random crypto!

#ሥርዓተ_ቅዳሴ_ዘሆሳዕና ክፍል ስድስት ከዚህ በኋላ ካህናት ቅዳሴ ይግቡ እንደተለመደው በም | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

#ሥርዓተ_ቅዳሴ_ዘሆሳዕና

ክፍል ስድስት

ከዚህ በኋላ ካህናት ቅዳሴ ይግቡ እንደተለመደው በምሥራቅ ሳይሆን በምዕራብ በር ይግቡ ሰራዒው ዲያቆን ከፊት  በስተምዕራብ በኩል ባለው በተዘጋው የቤተ መቅደስ በር ፊት ለፊት ቆሞ ሦስት ጊዜ በዕዝል ዜማ እንዲህ ይበል፡፡

ይ.ዲ አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት!
አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት!
አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት!

ካህኑም ቤተ መቅደስ ውስጥ በመሆን ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ በተዘጋው የቤተ መቅደስ በር ላይ ቆሞ በመቀበል እንዲህ ይበል!

ይ.ካ መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት!
መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት!

ከዛ በድጋሜ ሰይዒው ዲያቆኑ ቀጥሎ በድጋሜ ይበል!

ይ.ዲ አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት!
አርኅው ኆኃተ መኳንንት!
አርኅው ኆኃተ መኳንንት!

ካህኑ በድጋሜ ይህንን ይበል!

ይ.ካ መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት !
መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት!

በሦስተኛ ዲያቆኑ ይህንን ይበል!

ይ.ዲ እግዚአብሔር አምላከ ኃያላን
ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት!
እግዚአብሔር አምላከ ኃያላን ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት!

ከዚህ በኋላ ካህኑ የቤተ መቅደሱን መዝጊያ እየከፈተ እንዲህ ይበል!

ይ.ካ ይባዕ ንጉሠ ስብሐት" ይባዕ አምላከ ምሕረት

ቅኔ ማኅሌቱ ጋር ወረብ(ቸብቸቦ) በጥቂቱ ይበሉ!

ከዚህ በኋላ የቅዳሴው ጸሎት በዕለተ ሰንበት እንደ ተለመደው የቁርባን ሥርዓት ይፈጽሙ ቅዳሴው ስለዚህ ዕለት በዓል ዜና የሚናገር የቅዱስ ጎርጎርዮስ (የሆሳዕና ቅዳሴ) ነው!

ዘነግህ

ምስባክ

ንፍሑ ቀርነ በእለተ ሰርቅ:
በእምርት እለት በአልነ:
እስመ ስርአቱ ለእስራኤል ውእቱ:

    መገኛ #መዝ 70 :3

ትርጉም

በመባቻ ቀን በታወቀችው በአላችን:
መለከትን ንፉ ለእስራኤል:
ስርአቱ ነውና!

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን  ዕብ 9÷11- ፍ ም
ንፍቅ/ዲ  1ጴጥ 4÷1-12
ንፍቅ/ካ  ግብ፡ሐዋ 28÷11-ፍ ም

#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ!

       መገኛ #መዝ 8÷2

እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ:
በእንተ ጸላኢ :
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ:

#ትርጒም፦

ጠላትን ለማሳፈር ቂመኛንና ግፈኛንም: ለማጥፋት ከህፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ::

#የዕለቱ_ወንጌል፦

ዮሐ 5÷11-31

ቅዳሴ #ጎርጎርዮስ

አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join