Get Mystery Box with random crypto!

ከእናንተ የመጣ ጥያቄ 208 ጥያቄው? set leje degel sathehon bet meqedes g | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ከእናንተ የመጣ ጥያቄ 208

ጥያቄው?
set leje degel sathehon bet meqedes gebta masqedes techlalech?


መልስ

አትችልም!ማንኛዋም ሴት ቤተ መቅደስ መግባት አትችልም ! አደለም ሴት ወንድም እራሱ አይገባም! ቄስ ዲያቆን ክህነት ያለው ሰው ነው የሚገባው! መቼም ያመዋል እንዴ? እንደምትሉ አልጠራጠርም ግን መቅደስ የምትለዋ ቃል ናት ይህይ እንዲህ እንድናገር ያደረገችኝ?

ጥያቄሽ መሆን ያለበት ሴት ልጅ ድንግል ሳትሆን #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥ ገብታ ማስቀደስ ትችላለች ወይ?

ተብሎ ነበረ መጠየቅ ያለበት! በቤተ መቅደስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ሰፊ ልዩነት አለ! መቅደስ የሚባለው መንበሩ ያለበት ታቡቱ የሚቀመጥበት ሥርዓተ ቅዳሴ የሚከናወንበትና በመጋረጃ የሚሸፈነው ነው! ቤተ ክርስቲያን ሥንል ደግሞ የሴቶችም የወንዶችም የካህናትም መቅደስን ጨምሮ ያካትታልና ቤተ ክርስቲያን የሚለው ሴትን ስለሚያካትት ያንን ቃል መጠቀም ተገቢ ነው! በብዙ ሰው ዘንድ ቤተ መቅደስና ቤተ ክርስቲያን ስለሚምታታ እና 1 ስለሚመስላቸው ብዪ ነው እሺ! በተረፈ መልሱ አዎ ገብታ ማስቀደስም መቁረብም ትችላለች በቁርባንም ማግባት ትችላለች!(በተክሊል ግን አይቻልም)

መጠየቂያ
@Men_Lerdawobot


ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube Subscribe በማድረግ አዳዲስ መረጃ ይከታተሉ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

@seratebtkrstian


አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
@Men_Lerdawobot