Get Mystery Box with random crypto!

#ዘረኝነት_ሁላችንንም_የሚውጥ_ጨካኝ_ዘንዶ_ነው! 'በዘረኛ ማህበረሰብ ውስጥ ዘረኛ ያለ መሆን ብቻ | ሰንፔር ሚዲያ Sapphire Media

#ዘረኝነት_ሁላችንንም_የሚውጥ_ጨካኝ_ዘንዶ_ነው!

"በዘረኛ ማህበረሰብ ውስጥ ዘረኛ ያለ መሆን ብቻውን በቂ አይደለም:: ፀረ-ዘረኛ መሆንም አለብህ!" (Angela Davis)

ዘረኝነት እያንዳንዳችንንም የሚበላ አውሬ መሆኑን በዚህ አጭር ዘመን ተመልክተናል:: ዘረኝነት አንተ ዘረኛ ስላልሆንክ ርቆ አይቀመጥም:: ብሔርህን: ቀዬህን: ቋንቋህን ለይቶ እስከ ደጅህ ይመጣል:: ጳጳስ ስለሆንክ: ቄስ ስለሆንክ: ቢሾፕ ስለሆንክ: መጋቢ ስለሆንክ: ሼክ ስለሆንክ አይተውህም:: ቀን ጠብቆ: ቀየ ቆጥሮ አውሬው ደጅህ ይመጣል:: ከወለጋ: ከጋምቤላ: ከአፋር: ከቤንሻንጉል ስለራቅህ የምትተርፍበት ሰላማዊ ሥፍራ አይኖርህም:: ዘር ቆጥሮ የመግደል አቅም ያለው ቀን የሚጠብቅ ጨካኝ ዘረኛ ጎረቤትህ: መስሪያ ቤትህ: ስራ ቦታ: ቤተ ክርስቲያንህ: መስጊድህ ውስጥ አለልህ!!

የነፍሰ በላው ናዚ ጭፍጭፈ ካለፈ በኅላ በ1946 Martin Niemoller የተሰኘ የሉተራን ቄስ የተናዘዘው ታዋቂ አባባል አለ:: ይህ አባባል "መጀመሪያ ወደ ሶሻሊስቶች መጡ: ሶሻሊስት ስላልሆንኩኝ ምንም አልተናገርኩም ነበር:: ቀጥሎ ወደ ንግድ ማኅበር መጡ: የነጋዴዎች ማኅበር ውስጥ ስላልሆንኩኝ ምንም አልተናገርም ነበር:: ቀጥሎ ወደ አይሁዶች መጡ: አይሁድ ስላልሆንኩኝ ምንም አልተናገርም ነበር:: በመጨረሻም ወደ እኔ መጡ:: የሚጮህልኝ አንድም ሰው አልተረፈም ነበር" ይላል!!

Martin Niemoller ይህንን ያለው በናዚ ጭፍጭፋ ወቅት ምሁራን እና የቤተ ክርስቲያን ሰዎች የናዚን ጭፍጨፋ ላለመውገዝ ዝምታ በመምረጣቸው ምክንያት ነበር::

ብሔርተኛውን ሕገ መንግስት መሰረቱን ያደረገውና ላለፉት ሦስት ደርዘን አመታት ሲቀለብ ቆይቶ ኅይሉን በማፈርጠም እየበላን ያለው ዘንዶ በጊዜ ተባብረን ጮኸን ካላቆምነው እያንዳንዳችን ቤት መምጣቱ አይቀሬ ነው:: ያኔ የትምህርት ደረጃህ: የስራ ሁኔታህ: እምነትህ: የፖለቲካ አቋምህ: ስምና ዝናህ አያድንህም:: የዚያኔ በጠንካራ ግንብ የታጠረ ግቢ ውስጥ መኖርህ:: ዘመናዊ ፍጣን መኪና መንዳትህ አያድንህም!!

የሃይማኖት መሪ ነኝ:: ምሁር ነኝ:: ከተማና ገጠር ነኝ:: ሳትል በጊዜ መጮህ ያለብህ ለዚህ ነው:: ያለበለዚያ ልጆችህን: ቤተሰብህን: ዘመድ አዝማድህን: ወዳጆችህን አንተን "አልነካም" ባይን የሚበላ የዘር ዘንዶ እየመጣብህ ነው:: ቤተ መንግስት ብትሆን: ቤተ መቅደስ ብትሆን: መስጊድ ብትሆን: የባለስልጣን ቤተሰብ ብትሆን የትም ብትሆን አይምርህም!!

Alex Zetesat