Get Mystery Box with random crypto!

ጥላህን አንሣ ሰውዬው አሳ በማጥመድ ሙያው ተጠቅሞ የሚያጠምዳቸውን አሳዎች በመሸጥ ይተዳደራል።ዘው | Semeredin Shemsee

ጥላህን አንሣ

ሰውዬው አሳ በማጥመድ ሙያው ተጠቅሞ የሚያጠምዳቸውን አሳዎች በመሸጥ ይተዳደራል።ዘውትር ማልዶ ይኽንኑ ስራውን ስያከናውን ከእለታት አንድ ቀን ግን አሳዎች ወደ መቃጥኑ አልቀርብም በማለታቸው እጅጉን አዘነ።መቃጥኑን እያነሳ አንዴ ወደቀኝ አንዴም ወደ ግራ እያደረገ ደጋግሞ ቢጥለውም ትርፉ ድካም እንጂ አንድም የተያዘ ዓሳ አልነበረም።ከውኃው ዳር ሆነው የሰውዬውን ሁኔታ ሲከታተሉ የነበሩ አንድ የእድሜ ባለጸጋ ሰው ጠጋ ብለው ተገቢውን ሰላምታ ካቀረቡለት በኋላ ስለሰራው ጠየቁት እሱም ''ኧረ አባቴ የዛሬውስ አይወራ ይኸው እዚህ ከተገኘሁ ብዙ ሰዓት ቢያልፍም እስካሁን ግን አንድም ዓሳ ወደ መቃጥኑ ብቅ አላለም፤እኔ የምለው ዓሳዎቹ ዛሬ የት ገቡ?'' አለ ብስጭት ብሎና ተማሮ።ሽማግሌው ወደ ሰውዬው ጠጋ ብለው ''ዓሳዎቹማ የትም አልሄዱም ነገር ግን አንተ ጥላህን ጥለህባቸው በየት በኩል ይምጡ፤ትሰማኛለህ ወዳጄ ዓሳዎቹ ወደመቃጥኑ እንዲመጡ ከፈለክ ጥላህን አንሳላቸው'' አሉት ይባላል።