Get Mystery Box with random crypto!

‍ 'ሀፍሲ' ክፍል ሶስት ፀሐፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ ... ዴቭ ትክክለኛ ሰሙ ዳዉድ ነዉ። ዳዉድ ከ | || Sᴇʟʟᴜ ᴀʟʟᴇ ɴᴇʙɪʏ ﷺ ||

‍ "ሀፍሲ"
ክፍል ሶስት
ፀሐፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ

... ዴቭ ትክክለኛ ሰሙ ዳዉድ ነዉ። ዳዉድ ከመሆኑ (እስልምናን ከመቀበሉ) በፊት ዳዊት ነበር። አላህ ቀጥተኛዉን መንገድ የመራዉ ማህበራዊ ሚዲያ በሚጠቀምበት ወቅት የኡስታዝ አቡ ሀይደርን ትምህርት ተከታትሎ ነዉ። በተለይ ፖስተር ሀይሉ እና ኡስታዝ አቡ ሀይደር ያደረጉትን ሀይማኖታዊ ዉይይት በተመለከተ ጊዜ የእስልምና ትክክለኛነት ተገለጠለት። በቤተሰቦቹ ከፍተኛ ጫና ቢያድርበትም እስልምናን ከተቀበለ በኃላ እስላማዊ ዒልምን በማደን የእዉቀት አድማሱን አስፍቷል። አሁን ደግሞ ኸይር ስራዎች ላይ ለመሳተፍ የዐመሉን ሷሊህ ጀመዓ አባል ሆኗል።

ክፍት ወደሆነዉ ወንበር ሲቀመጥ ከሀፍሲ ፊት ለፊት ነበር። ሀፍሲን የሆነ ቦታ አይቷታል ነገር ግን የት እንዳያት ማስታወስ አልቻለም። ትዝ የሚለዉ ነገር እሷን ባያት ጊዜ አጠገቡ ለነበረዉ ጓደኛዉ ቆንጆ እንደሆነች ነግሮታል።

ሸኽ አጃኢቡ "እንግዲህ ሁሉም ተሟሉማ አደል?" አሉ ኡስማንን እያዩ። አይኑን ከሀፍሲ ላይ አልነቀለም። እሷም በተመሳሳይ በአይኗቿ ዴቭን አልተፍታችዉም።  "አዎ ተሟልተዋል። እንጀምር..." አለና "ለአዲሱ አባላችን ራሳችንን እናስተዋውቅና ሹራችንን እንጀምራለን" ብሎ ራሱን ማስተዋወቅ ጀመረ። "ኡስማን እባላለሁ በሒሳብ አያያዝ (አካዉንቲንግ) የመጀመሪያ ድግሪ ሲኖረኝ አሁን ላይ በንግድ ስራ ተሰማርቻለሁ።" ከሱ በመቀጠል የሀፍሲ ተራ ነዉ። ዴቭ የዚችን ዉብ ልጅ ማንነት ለማወቅ ጓጉቷል። "ሀፍሷ እባላለሁ። የክሊኒካል ፋርማሲ ተመራቂ ተማሪ ነኝ" በጣም አጭር ነበር። ዴቭ ማወቅ የፈለገበት ድረስ አልተጓዘችም። የትዳር ሁኔታ መገለጽ ነበረበት። ሁሉም በየተራ ራሳቸዉን ካስተዋወቁ በኃላ ኡስማን "በመጨረሻ አዲሱ የጀመዓችን አባል ራሱን ያስተዋውቀናል" በማለት እድሉን ለዴቭ ሰጠዉ።

"ዳዉድ እባላለሁ። ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ በኮምፒዉተር ሳይንስ የተመረቅኩ ሲሆን አሁን በግል ድርጅት ዉስጥ ተቀጥሬ በመስራት ላይ እገኛለሁ።" በተመሳሳይ ሁኔታ ሀፍሲ ማወቅ የፈለገችዉን ዴቭ አልገለጸም። "ምናልባትም ባለትዳር ይሆናል" ብላ አሰበች።

.
.
.

"ደስ የሚል ጀመዓ ነዉ። እናንተን በመተዋወቄ ደስ ብሎኛል።" አለ ዴቭ። ከቢሮ እንደወጡ ሳሪ ዴቭንና ሀፍሷን አስተዋውቃቸዋለች። ስማቸዉን ድጋሜ ከመተዋወቅ የዘለለ ግን ሌላ ነገር አላወሩም።

"ሳሪ ወደ ሰፈር ነሻ?"
"አዎ ዴቭ ትሸኘናለህ?" አለችዉ የሀፍሲን ፍቃደኝነት ለማወቅ ወደሷ እየተመለከተች
"እኔም ወደሰፈር ነኝ። አብረን እንሂድ!" ብሎ መኪናዉን ከፈተላቸዉ።

"ዱሩን ገደሉን ባህሩን ጥሼ
ጥሪ ደርሶኛል ልምጣ መልሼ
የጉድጓዱን ጥግ ያን አስፈሪዉን
ያልፈዋል እግሬ ጥቁር ዋሻዉን
አልፈራም አልፈራም ........" ለስራና ለወኔ የሚያነሳሳዉን ተወዳጅ ነሽዳ በትንሹ ተከፍቶ እያዳመጡ ነዉ። ከሶማሌ ተራ ተነስተዉ ወደ ጦር ሀይሎች እያመሩ ነዉ። ሀፍሲ ምን እንደምታወራ ግራ ገብቷታል። ከኃለ ወንበር ሁና በመኪናዉ ስፖኪዮዎ በጨረፍታ ትመለከተዋለች። እሱም በተመሳሳይ ቀና እያለ ያያታል። በጣም ተፈራርተዋል። ድንገት አይኖቻቸዉ ሲገጣጠሙ ሁለቱም በድንጋጤ ያቀረቅራሉ። መተያየታቸዉ ያቁም እንጂ ልቦቻቸዉ የተገጣጠሙ ይመስላሉ።

... ለማፍቀር ማሰብ አያስፈልገዉም። ፍቅር በተፈጥሮ የሚለገስ ቅጽበታዊ የልብ መሻት ነዉ። አዎ! ሀፍሲ በጣም ብዙ ወንዶችን ታዉቃለች። በጓደኝነትም፣ ለትዳርም የሚመጡ አያሌ ናቸዉ። ነገር ግን ስለ ፍቅርም ሆነ ስለ ትዳር አስባም ሁና አልማ አታዉቅም። ከኡስማን የጋብቻ ጥያቄ ዉጭ ሁሉንም ፊት ለፊት እንደማትፈልጋቸዉ ነግራቸዋለች። የኡስማንን ጥያቄ ግን አሁንም አልመለሰችለትም።

ከሹራዉ ከመዉታቸዉ በፊት ሸኽ አጃኢቡ በጣም አስቸኳይ ለሆነ ሀጃቸዉ ፈልገዉት ኡስማን ሀፍሲን የማናገር እድል አላገኘም። አራት ወር ሙሉ ሲጠብቀዉ የነበረዉን የጋብቻ ጥያቄ መልሱን ሳያዉቀዉ አሁንም ሌላ ቀን ሊያስቆጥር ነዉ።

"ዴቭ እዚህ ልዉረድ ሀፍሲ ቤተል ስለሆነች እሷን ሸኛት። ደሞ ትዛዝ ነዉ።" ብላ እየሳቀች ከመኪናዉ ልትወርድ ስትል ሀፍሲ "ኧረ አታስቸግሪዉ በታክሲ መሄድ እችላለዉ።" አለች ለመግደርደር ያክል ነበር።
"በይ አትቅበጪ አዝዤዋለሁ ያደርስሻል"
"ታዛዥ ነኝ አለቃ!" የዴቭ መልስ ነበር።

ከፒያሳ ጀምረዉ ጦርሀይሎች እስከሚደርሱ ሳሪ ብቻ እያወራች ነበር። አሁን ግን ሳሪ ወርዳለች። ዴቭ በዝምታ ሊያስደብራት አልፈለገም።

"ዝምተኛ ነሽ ልበል። ጓደኛሽንኮ በወሬ አላገዝሻትም።" ወሬ ለመጀመር ያክል እንጂ እየፈራ ነበር።
"አይ ዝምተኛ እንኳ አይደለሁም!" አጭር መልስ ደነገጠ። የማዉራት ፍላጎት አይኖራት ይሆናል ብሎ በማሰብ በደጋሜ ፈራ ተባ እያለ "ያዉ የኔ ስራ ካንቺ ጋር ያገናኘዋል መሰል። የኮምፒዉተር ባለሙያ ስለሆንኩ የጀመዓዉን ስራዎች በማህበራዊ ሚዲያ ማስተዋወቅና ገንዘብ ማሰባሰብ ነዉ"
"ልክ ነህ በጥሩ ሁኔታ እንደምሰራ ተስፋ አደርጋለሁ!" ሀፍሲ ስለጀመዓዉ ከልቧ ትጨነቃለች። ሰዉ መርዳት ያስደስታታል። የተቸገሩ ሰዎች በሷ ምክንያት ሲያገኙ፤ ለተከፉ ሰዎች የሳቅና የደስታ ሰበብ መሆን ሁሌም ምትመኘዉ ነዉ።
"ኢንሻ አላህ ከአላህ ጋር ጥሩ እሰራለሁ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ አንዳንድ መረጃዎች ካንቺ እፈልጋለሁ"
"እዚጋ ልዉረድ?" አለችዉ። ደነገጠ። ከጦር ሀይሎች ቤተል ቅርብ መሆኑን ዘንግቶት ብዙ እንጓዛለን ብሎ አስቦ ነበር። መኪናዉን የመንገዱን ዳር ካስያዘ በኃላ ወደሷ ዙሮ በደንብ አያት እዉነትም ዉብ ነች። "ጨረቃ የጥቁሩ ሰማይ ድምቀት እንደሆነችዉ ሁሉ ሀፍሲ ለዚች አለም ዉበት ናት።" ብሎ አሰበ።
"ስልክ ቁጥርሽን ስጭኝና ሚያስቸግረኝ ነገር ካለ እየደወልኩ እጠይቅሽለሁ።"

ክፍል አራት ይቀጥላል......

SHARE
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
JOIN: @SELLU_RESUL
JOIN: @SELLU_RESUL