Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄ፦ በምክንያትም ይሁን ያለ ምክንያት የጀናባን ትጥበት ማዝግየት ብይኑ ምንድነው? መልስ፦ የ | የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

ጥያቄ፦ በምክንያትም ይሁን ያለ ምክንያት የጀናባን ትጥበት ማዝግየት ብይኑ ምንድነው?

መልስ፦ የሶላት ወቅት እስካልደረሰ ድረስ ችግር የለውም። የሶላት ወቅት ከደረሰ ታጥቦ ሶላቱን መፈፀም ግድ ይለዋል። ለምሳሌ ዙህርና 0ስርን ይመስል። ረፋድን በተመለከተ ግን ለምሳሌ ዙህር ላይ እስከሚታጠብ ድረስ ቢዘገይ (ችግር የለውም።) ሶሒሕ አልቡኻሪና ሙስሊም ላይ ሑዘይፋና አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሐዲሥ እነሱ ነብዩን ﷺ ሲያገኙ ይሰውራሉ። ነብዩ ﷺ "ምንድነው ነገራችሁ?" ሲሏቸው "ጀናባ ላይ ነበርንና ጦሀራ ላይ ሳንሆን አብረንህ መቀመጥን ስለጠላን ነው" አሉ። በዚህን ጊዜ ነብዩ ﷺ "ሙስሊም አይነጀስም" አሉ። እና ያለ ጦሀራ መቆየታቸውን አልነቀፉም። አላህ ሆይ! በሳቸው ላይ ሶላትህን አውርድ።

ከሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ ፈትዋ የተወሰደ
ምንጭ፦ https://binbaz.org.sa/fatwas/15618/%D9%85%D8%A7-%D8%AD%D9%83%D9%85-%D8%AA%D8%A7%D8%AE%D9%8A%D8%B1-%D8%BA%D8%B3%D9%84-%D8%A7%D9%84%D8%AC%D9%86%D8%A7%D8%A8%D8%A9

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor