Get Mystery Box with random crypto!

ሙመይዓዎች አንድ ሰው 'ሙብተዲዕ ነው' ተብሎ ብይን ሊሰጥበት (ኢጅማዕ) የዓሊሞች የጋራ ስምምነት | የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

ሙመይዓዎች አንድ ሰው "ሙብተዲዕ ነው" ተብሎ ብይን ሊሰጥበት (ኢጅማዕ) የዓሊሞች የጋራ ስምምነት መስፈርት ነው በማለታቸው ላይ የተሰጠ መልስ
–––––
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሓዲ ዑመይር አል-መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) እንደሚከተለው ተጠየቁ:- የቢድዓ ባለቤትን በማነወር (ሙብተዲዕ ነው ብሎ ብይን በመስጠት) ላይ የዓሊሞች የጋራ አቋም መኖሩ መስፈርት ይደረጋልን? ወይስ የአንድ ዓሊም ንግግር በቂ ነው?

የሸይኽ ረቢዕ (ሀፊዘሁላህ) መልስ:- ይህች -ባረከላሁ ፊኩም- ቆሻሻ ከሆኑ የሙመይዓዎች መርሆ ነች። በየትኛው ዘመን ላይ ነው የዓሊሞች የጋራ አቋም መስፈርት የሆነው?? ለዚህ መስፈርት ማስረጃውስ ምንድነው?? ምክንያቱም የትኛውም በአላህ መፅሃፍ (ቁርኣን) ውስጥ የሌለ መስፈርት መቶ (100) መስፈርት ቢሆን እንኳን ውድቅ ነው።

አሕመድ ኢብኑ ሀንበል አለያም የህየ ኢብኑ መዒን አንድን ሙብተዲዕ ካነወሩ ዓለም ላይ ያሉ ሱኒዮች ተሰባስበው ይህ ሰው ሙብተዲዕ በመሆኑ ላይ የጋራ አቋም እስከሚይዙበት "አይሆንም" ልላቸው ነው?

ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው ላይ "ይህ ሙብተዲዕ ነው" ካሉ ሁሉም ነገር አበቃ። ኢማሙ አህመድ ይህ ሙብተዲዕ ነው ካሉ ሰዎች ሁሉ ተቀብለው ከኋላቸው ይከተላሉ። ኢብን መዒን "ይህ ሰው ሙብተዲዕ ነው" ካለ አንድም የሚጨቃጨቀው አልነበረም።

የጋራ አቋም መስፈርትነትማ ግዴታ በሁሉም ሸሪዓዊ ህግጋት ላይ ሊሆን የማይችል ነገር ነው። ጥሩ፣ ለምሳሌ:- ሁለት ምስክሮች አንድ ሰው ላይ ሰው በመግደሉ ለመመስከር ቀረቡ፣ ግዴታ ሁሉም ሙስሊም ያ ሰው ገዳይ እንደሆነ መስማማቱን መስፈርት ሊደረግ ነው? አንድ ዳኛ የሆነ ሰው ገዳይ በሆነ ሰው ላይ የአላህን ህግ "ካሳ በማስከፈልም ሆነ የገደለን እንዲገደል" የአላህን ህግ እንደወረደ ተፈፃሚ በማድረግ ረገድ የሙስሊሙን ማህበረሰብ መስማማት (የጋራ አቋም) መያዝ ግዴታ ልናደርግበት ነው? ይህ ሙብተዲዕን ሙብተዲዕ ከማድረግ የከፋ ነውን?

እነዚያ እኮ (ኢጅማዕ መስፈርት ነው የሚሉት) የባጢል ባለ ቤት የሆኑ ሙመይዓዎች ናቸው። በደፈረሰ ውኃ ውስጥ የሚያድኑ የሸር ሰባኪያን ናቸው። እንዲህ ያሉ ውዳቂ ነገሮችን አትስሙ!።

አንድ እውቀት ያለው ሚዛናዊና ታማኝ ዓሊም አንድን ግለሰብ ካነወረ ይህን ያነወረበትን ነገር ወይም ማነወሩን መቀበል ግድ ነው። ይህ ዓሊም ያነወረውን ሌላ ሚዛናዊና ታማኝ የሆነ ዓሊም በተቃራኒው ከቀደሰው ይህን ጊዜ ሁለቱም በዚያ ግለሰብ ላይ የሚሉትን ነገር እናጠናለን፣ የዚህ ማነወርም በደንብ ይጠናል የሌላኛው መቀደስም በደንብ ይጠናል። ማነወሩ ግን የተብራራና ግልፅ የሆነ ከሆነ ከሚቀድሰው ይልቅ ምንም ያህል የቀዳሾች ቁጥር ቢበዛ እንኳ የዚህ ማነወር ይቀደማል (ከቀደሰው ዓሊም ይልቅ ያነወረው ዓሊም ተቀባይነት ይኖረዋል) ለምሳሌ:- አንድ ዓሊም በተብራራና ግልፅ በሆነ መልኩ አነወረ፣ ሌሎች 20 (ሀያ) እና 50 (አምሳ) የሚሆኑ ዓሊሞች በተነወረው ሰው ላይ ከመልካም ግምትና ግለሰቡ ከላይ ከሚያንፀባርቀው ነገር የዘለለ ማስረጃ ሳይኖራቸው ተቃርነውት ቢቀድሱት፣ ያ ዓሊም ደግሞ በማነወሩ ማስረጃ ካለው ይህ አነዋሪው አካል ማነወሩ ይቀደማል፣ ምክንያቱም በማነወሩ ላይ ማስረጃ አለው፣ ተቀዳሚው ማስረጃ ያለው አካል ነው። ምድርን የሚሞላ ፍጡር ሁሉ ቢቃረነው የሚቀደመው ማስረጃና ማስረጃ ያለው ነው።

ማስረጃው ከእርሱ የሆነ አካል ሐቁም ከእርሱ ነው። ጀመዓ ማለት ብቻውን ቢሆን እንኳን ሀቅ ላይ ያለ ነው። አንድ ሰው በሱና ላይ ቢሆንና የሁለት አለያም የሶስት ከተማዎች ባለ ቤት የሆኑ ሰዎች ሁሉ ቢቃረኑትና ሙብተዲዕ ቢሆኑ ሀቁ ብቻውን ከሆነው ሰው ጋር ነው። እርሱ ዘንድ ያለው እውነትና ማስረጃ ሌሎች ዘንድ ካለው ባጢል ይቀደማል። ሐቅን እና ግልፅ የሆነን ማስረጃ ማክበር ግዴታችን ነው።

قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

«እውነተኞች እንደሆናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ፣ በላቸው፡፡» አል-በቀረህ 111

وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ مَن فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ

«በምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡» አል-አንዓም 116

ጥቂት ሰዎች ቀርተው ምድር ላይ ያለው ሰው ሁሉ ያለ ማስረጃ ባጢል ላይ ቢስማማና በአንድ ነገር ላይ የጋራ አቋም ቢኖረው እንኳ ከማስረጃ የተራቆተች ብዛት ከሆነች ለብዛታቸውም ሆነ ለአቋማቸው ምንም አይነት ግምት የላትም!።

የባጢል ባለ ቤቶችን የሚቃረናቸውና በማስረጃ የሚሟገታቸው ሰው ብቸኛ ቢሆን አለያም ቁጥራቸው አናሳ ቢሆኑ እንኳን ግምት የሚሰጠው ማስረጃ ላላቸው የሀቅ ተከታዮች ነው እንጂ የባጢል ሰዎች ቁጥራቸው በዝቶ ምድርን ቢሞላም ግምት አይሰጣቸውም። አላህ! አላህ! ሀቅን በማወቅና በሀቅ ላይ በመጣበቅ አደራ! በተለይ ማስረጀ የሚደገፍለት ከሆነ ሐቁን በመከተል ላይ አደራ!። አላህ ሁሉንም ለመልካም ነገር ይግጠም!! [ሚን ሸሪጢ መንሀጅ አትተምይዕ ወቀዋዒዱሁ ሊ-ሸይኽ ረቢዕ]
ትርጉም:- ኢብን ሽፋ: ረቢዐ ሳኒ 22/1443 ዓ. ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa