Get Mystery Box with random crypto!

ቶኪዮ አዲስ ባበለፀገችው መተግበሪያ የተነሳ ቱሪስቶች እየጎረፉላት ነው ተባለ ቶኪዮ በሚገኝ ባቡ | ሰሌዳ | Seleda

ቶኪዮ አዲስ ባበለፀገችው መተግበሪያ የተነሳ ቱሪስቶች እየጎረፉላት ነው ተባለ

ቶኪዮ በሚገኝ ባቡር ጣቢያ ውስጥ የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን ከሚናገሩ ቱሪስቶች ጋር ገጽለገጽ በመተያየት የሚተርጉም የስክሪን አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በሴቡ ሺንጁኩ ባቡር ጣቢያ ፖሊግሎት የሚል መጠሪያ የተሰጠውና የገጽለገጽ መተያያ የመተርጎሚያ ስክሪን  1ሜትር በ40 ሳንቲሜትር ቁመት ያለው ሲሆን፤ በባቡር ጣቢያው ማዕከላዊ ስፍራ ላይ በምትገኝ አስተናጋጅ ድጋፍ ሰጪነት የውጭ ዜጎች የሚናገሩትን ቋንቋ ወደ ጃፓንኛ፤ የጃፓንኛውን ደግሞ እነሱ ወደሚናገሩት ቋንቋ በድምጽ እያሰማ በጽሁፍ ደግሞ ስክሪን ላይ ተርጉሞ እያሳየ በቀላሉ እንዲግባቡ አስችሏል፡፡

ጃፓን፤ በ12 የተለያዩ ቋንቋዎች የበለፀገውን የመተርጎሚያ ቴክኖሎጂ በባቡር ጣቢያው ውስጥ በመጠቀሟ በተግባቦት ችግር ምክንያት የሚቀሩ ቱሪስቶች እንዳይኖሩ ከማድረጉም በላይ ለጉብኝት የሚሄዱ የውጭ ዜጎችን ቁጥር እንደሚሳድገው የNHK ዘገባ አመልክቷል፡፡