Get Mystery Box with random crypto!

ከገበሬው የምርት ስርጭት አገልግሎት ተጀመረ። ፐርፐዝ ብላክ ኢትኤች ትሬዲን ከገበሬው የምርት ስ | ሰሌዳ | Seleda

ከገበሬው የምርት ስርጭት አገልግሎት ተጀመረ።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትኤች ትሬዲን ከገበሬው የምርት ስርጭት አገልግሎት በዛሬው እለት አስጀምሯል፡፡ የፕሮጀክት ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሰናይት አየለ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደተናገሩት ከገበሬው ምርት ስርጭት አገልግሎት በዋናነት የግብርና ምርቶችን ከገበሬው በቀጥታ ወደ ሸማች ቤት ለቤት አቅርቦትን ጨምሮ የሚያካትት ነው፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ሸማቾች የአባልነት ቅጽ በመሙላት በቋሚነት ተጠቃሚ የሚሆኑበት በፈለጉት መጠን ምርት የሚያገኙበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ምርቶችም በዚሁ ስርአት ለሸማቹ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡ በሁሉም የአዲስ አበባ ክ/ከተሞች ይህን ግብይት የሚመሩ ሀላፊዎች መመደባቸውን እና መዋቅሩም እስከ ወረዳ የተደራጀ መሆኑን ወ/ሮ ሰናይት ተናግረዋል፡፡

በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ1400 በላይ ሰዎች የሸማች አባልነት ቅጽ መሙላታቸው የተገለጸ ሲሆን ከ1000 በላይ ዜጎችም በኤጀንትነት የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ የክፍያ ስርአቱም በሞባይል ባንኪንግ ፤ በባንክ ፤ በቴሌብር እና እጅ በእጅ ይሆናል፡፡ ፕሮጀክቱን ወደፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት እና በዱቤ ለመስጠት መታቀዱን ወ/ሮ ሰናይት አስረድተዋል፡፡

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ