Get Mystery Box with random crypto!

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በመጀመሪያ ሩብ ዓመት 377.4 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ ብ | ሰሌዳ | Seleda

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በመጀመሪያ ሩብ ዓመት 377.4 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ2015 የመጀመሪያው ሩብ የበጀት ዓመት ዘጠኝ የሎተሪ ዓይነቶችን ለገበያ በማቅረብና ከዕድል ጨዋታ ኮሚሽን 377.4 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል። በሦስት ወራት ውስጥ ዘጠኝ የሎተሪ ዓይነቶችን ለገበያ በማቅረብና ከዕድል ጨዋታ ኮሚሽን ለማግኘት ከታቀደው 91.6 በመቶውን ማሳካት ተችሏል።

በዚህም አስተዳደሩ በአጠቃላይ የተጣራ 136.1 ሚሊዮን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን፣  በሩብ ዓመቱ የእቅዱን 148 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ አሳውቋል። ይህ የገቢና የትርፍ መጠን ብሔራዊ ሎተሪ በሩብ በጀት ዓመቱ ለሽያጭ ባቀረባቸው ዘጠኝ የሎተሪ አይነቶችና ከዕድል ጨዋታዎች ኮሚሽን በሚያገኘው ገቢ ሲሆን፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር አዲስ ያስጀመረውን አድማስ የአጭር መልዕክት የሞባይል ሎተሪ የተገኘውን ገቢ አያካትትም።

ከአድማስ ሎተሪ ከሚገኘው ገቢ 25 በመቶውን ኢትዮ ቴሌኮም 75 በመቶውን ደግሞ ብሔራዊ የሎተሪ አስተዳድር የሚወስድ ሲሆን፣ ከፋይናንስ ጋር ያሉ የሲስተም ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው በዚህ ሩብ የበጀት ዓመት ከአድማስ ሎተሪ የተገኘውን ገቢና ትርፍ ለመናገር እንደማይቻል ተነግሯል።