Get Mystery Box with random crypto!

በባለፈው ጦርነት የወሎን ህዝብ ያክል መስዋዕትነት የከፈለ መከራና ስቃይ ያየ የለም ። በዚህኛውም | Seid Social

በባለፈው ጦርነት የወሎን ህዝብ ያክል መስዋዕትነት የከፈለ መከራና ስቃይ ያየ የለም ። በዚህኛውም ጦርነት የጦርነቱ አውድማ እንዲሆን የተመረጠው ወሎ ነው ። ወሎ የኢትዮጵያን መከራ እንዲሸከም የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ እየተነባበረ ህዝባችንን እያመሰቃቀለው ነው ።

የአማራ ክልል መንግስት እንደሆነ ለወሎ ብዙም ደንታ እንደሌለው ትላንትም አይተነዋል ዛሬም እያየነው ነው ።

መሆን ያለበት የወሎ ህዝብ ማንንም ሳይጠብቅ ከመከላከያ ሀይላችን ጎን ተሰልፎ ደጀንና ጋሻ ሆኖ ወራሪውን ሀይል እስከመጨረሻ መታገል ነው ። ህዝባችን ከባለፈው ስብራት ሳያገግም ዛሬም እንደገና ሌላ ስብራት መጥቶበታል ። በመሆኑም ሳንሰበር እንታገል ።

ስንታገል ከምንከፍለው መስዋዕትነት በላይ ሳንታገል የምንከለው ዋጋ በእጅጉ ይከፋልና አሁንም ከሰራዊታችን ጎን ሆኑን እንታገል !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial