Get Mystery Box with random crypto!

#ለሰላም_ከሆነ_አዎ_አሽቃብጣለሁ ሲናቅ ዝም ካልኩኝ ያብሮ አደጌ ማተብ ሲጣስ ዝም ካልኩኝ የቤተ | የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#ለሰላም_ከሆነ_አዎ_አሽቃብጣለሁ
ሲናቅ ዝም ካልኩኝ ያብሮ አደጌ ማተብ
ሲጣስ ዝም ካልኩኝ የቤተስኪያን  አደብ
ያ ሰው ሰነባብቶ  ሴራ በመሰብሰብ
የኔንም መስገጃ  ይቀማኛል  በደንብ

አየህ አይከብደኝም ነግበኔዬን ማሰብ

በዳይ  ቢሆኑ እንኳ እናትና አባቴ
ከተበዳይ ጎን ሁን ብሎኛል እምነቴ
ታዲያ
ቤተ እምነት ታውኮ ሀዘን ባጠላባት
ኦርቶዶክሱ ጓዴ  አንገት በደፋበት
በዚህ የቀን ጥቁር
በምችለው ካልቆምኩ ካልሆንኩኝ ከጎኑ
        ምኑ ላይ  ሰው ሆንኩኝ
ብሶቱ ካልባሰኝ  ካልገባኝ  ሀዘኑ
እናም እልሀለሁ......
በኔ ካልደረሰ ምን አገባኝ  እኔ
ብዬ ዝም አልልም ይሄን አረመኔ
ህመሙ ያመኛል ኦርቶዶክስ ወገኔ
ደግሞ.....
ሰላም ከጠፋኮ  ግማሽ ወገን ታሞ 
ለኛም ይቸግራል
ከመስጊድ  ለመስገድ በጀመአ ቁሞ
#ሼን