Get Mystery Box with random crypto!

በምነቴ ሙስሊም ነኝ_ በማንነቴ ሰው          ኦርቶዶክስ ወንድሜን  ሲከፍው የማልወድ _ ሆዴ | የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥


በምነቴ ሙስሊም ነኝ_ በማንነቴ ሰው
         ኦርቶዶክስ ወንድሜን 
ሲከፍው የማልወድ _ ሆዴን የሚብሰው
" አዎ ሰው ነኝ እኔ "
ግፍን ለመቃወም _ በደልን ለማውገዝ
በኔ ካልደረሰ _  ብዬ ዘር የማልመዝ
ያንተ ቤት ሲንኳኳ _ ይሰማል እኔም ቤት
ነው እና ከድሮም _ ያገሬ ሰው  ተረት
ዛሬ የኦርቶዶክስ _ ቤተ እመነት ሲታመስ
ዝም ብዬ ባልፍ _  ደርሶ በማድበስበስ
ነገ ይቀጥላል _  የኔ _መስጊድ ድረስ
እናም እጮሀለሁ ...
ስቃይ እንግልቱን  _ ግፉን ተቃውሜ 
ኦርቶዶክስ ወገኔን _ አግዛለሁ ባቅሜ
ቤተ እምነት መተንኮስ _ ነውና አገር ማፍረስ
እባካችሁ ተው  _  ብዙ ደም እንዳይፈስ
#ሼን