Get Mystery Box with random crypto!

...... አላጋጠማችሁም....... ድንገት ወደ ሂወታችን ይገቡና አርፎ የተኛ ልባችንን ይቀሰቅሱታ | የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

...... አላጋጠማችሁም.......
ድንገት ወደ ሂወታችን ይገቡና አርፎ የተኛ ልባችንን ይቀሰቅሱታል ፣ በተስፋ ይሞሉናል ፣በምኞት እሩቅ ያሳዩናል ፣ምርኩዝ የሆኑ መስለው እጃችንን አጥብቀው ይይዙታል ፣ያን ሰሞን ሆን ብለው ቀድሞ የማናውቀውን አለም ያሳዩናል ያው ሰው አይደለን እኛም ቀን ቀንን እየተካ ሲሄድ ያ አርፎ የተኛ ልባችን ዳግም ይቀሰቀሳል ፡ትናንትናውን ረስቶ አዲስ የሂዎት መንገድ ይጀምርና ፡ አሻግሮ ነገውን ያልማል፡ አጥብቆ የያዘን እጃቸው የማይለቀን የማይተወን መስሎን ሙሉ እኛነታችንን እነሱ ላይ እንጥላለን ፡ እነሱን እንደገፋለን .... ያን ጊዜ ድንገት እንደመጡት ድንገት ምስስ ብለው ከሂወታችን ይወጣሉ... ውረድ ብንለው በዋዛ የማይወርድ የትዝታ ጓዝ አሸክመውን ፡ የማይመለስ ጥያቄ ሰጥተውን እንዲህ ነው ብለው እንኳ ምክኒያታቸውን ሳይነግሩን ድንገት እንደገቡት ድንገት ጥለውን ይወጣሉ ...