Get Mystery Box with random crypto!

'ታሳዝነኛለች' ለሷ እንደማይሆናት _ውስጧ ይነግራታል ወስና እንዳትሄድ_ ፍቅሯ ይይዛታል | የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

"ታሳዝነኛለች"
ለሷ እንደማይሆናት _ውስጧ ይነግራታል
ወስና እንዳትሄድ_ ፍቅሯ ይይዛታል
ደግሞ ባንድ በኩል _እድሜዋን ስታስብ
በቁጭት በንዴት _ ትላለች እንግብግብ
ልቧ እየዋለለ _ በመሄድ በመቅረት
ትርጉሙ ጠፍቶባት_ የመንጋት የመምሸት
ከደስታ ተኳርፋ _ ሂዎት ትገፋለች
ይቺ አይነት አፍቃሪ _ ታሳዝነኛለች
#ሼን