#ይቅርታ...... እንዲያ ላፈቀርኩሽ _ ከራሴ አስበልጬ ስርሽ ስርሽ ላልኩት _ አንቺኑ መ | የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
#ይቅርታ......
እንዲያ ላፈቀርኩሽ _ ከራሴ አስበልጬ
ስርሽ ስርሽ ላልኩት _ አንቺኑ መርጬ
የግሌ ላደርግሽ _ እየተፍጨረጨርኩ
ያለፍላጎትሽ _ አንቺን ስላደከምኩ
ይቅርታ ......
ስትዋሺ አምኜ _ ስትንቂኝ አክብሬ
እየተለማመጥኩ _ ከጎንሽ አድሬ
እስክትሰለቺኝ _ ችክ ስላልኩብሽ
ግድ የኔ ሁኝ ብዬ _ ለተለጠፍኩብሽ
ስላለፈው ሁሉ _ ፍቅሬን ስል ላረኩት
ይቅርታ አድርጊልኝ _ ትናንት ለሰራሁት
ዛሬ ሄጃለሁኝ _ አረብሽም ዳግም
መቸም አልመለስ _ ካለሽበት ግድም
#ሼን