Get Mystery Box with random crypto!

#የተሻሻለ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥ | Sans peurs

#የተሻሻለ

የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ መስፈርቶች ላይ ማሻሻያ ተደርጎበታል።

የመመዝገቢያ መስፈት የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

• ለአዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ)

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 375፣ ለሴት 370
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 365፣ ለሴት 360

• ለሌሎች ክልሎች

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 380 ፣ ለሴት 375
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 370፣ ለሴት 365

የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 እስከ 30/2014 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ይጠናቀቃል ተብሏል።

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

የመግቢያ ፈተናው መጋቢት 07/2014 ዓ.ም ይሰጣል። (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia