Get Mystery Box with random crypto!

#ASTU #AASTU ሁለቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ | Sans peurs

#ASTU #AASTU

ሁለቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስገባ ነጥብ ያዝመዘገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ በዛሬው እለት አውጥተዋል።

የመመዝገቢያ መስፈርቱ የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት ከዚህ በታች እንደተገለፀው ነው።

ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤ/ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ) ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 395 ለሴት 390
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 385 ለሴት 380


ለሌሎች ክልሎች ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 400 ለሴት 395
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 390 ለሴት 385


የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ከላይ የተቀመጠውን የምዝገባ መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች በማንኛውም ስፍራ ሆነው በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

ፈተናው መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚሰጥ ተነግሯል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia